ጥብቅ ፍተሻ ቢበዛ ባይበዛ የነፃነት ቀንን አያስቀረውም !

በአዲስ አበባ ፍተሻው ዛሬም እደቀጠለ ነው አለም ባንክ የነበረው ፈተሻ ፈረንሳይ ለጋሲዎን ደርሷል። ፈረሳይ ለጋሲዎን አካባቢ መንገድ ዝግ ነው መኪናም ሆነ ሰው ማለፍ አይችልም። (ዘ-ሐበሻ) ዛሬ በአዲስ አበባ አደባባዮች ማምሻውን ፍተሻ ተጀመረ:: ፍተሻው እስከማክሰኞ ምሽት ድረስ እንደሚቀጥል የፖሊስ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታውቀዋል:: እንደ ፖሊስ ምንጮች ገለጻ ከሆነ ሕወሓት የሚመራው መንግስት የጸጥታ ስጋት አለብኝ በሚል በአዲስ አበባ ዛሬ ማምሻውን ፍተሻ የጀመረ ሲሆን ፖሊሶችም በቀን 12 ሰዓታት እየሰሩ ነው:: በምሽት ከ4 እስከ 5 ሰዓት የሚቆይ ፍተሻ አድርጉ ተብለው ትዕዛዝ የወረደላቸው ፖሊሶች በተመረጡ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የጀመሩትን ፍተሻ እስከ ማክሰኞች ምሽት ድረስ ይቀጥላሉ ተብሏል:: ሕወሓት የሚመራው መንግስት በአዲስ አበባ የሚከበረውን የመስቀል በዓል ተከትሎ የሆነ ነገር ሊፈጠር ይችላል በሚል ለፖሊሶች ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ያስታወቁት የፖሊስ ምንጮች በየሰፈሩ በሚደረጉ የደመራ ቦታዎችንም በአይነቁራኛ እንዲከታተሉ መታዘዙን አስታውቀዋል:: ዛሬ ማምሻውን የተጀመረውን ፍተሻ ተከትሎ ሕዝብ እየተሸበረ መሆኑም ታውቋል:: አንዳንድ ፖሊሶች በተለይ ሕዝቡን እያመናጨቁ እንደሚፈትሹ የደረሱን መረጃዎች ጠቁመዋል:: Source:: zehabesha

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *