ዛሬም ለበጎቻቸው ራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ እውነተኛ እረኞች አሉ። ከደረጄ ሀብተወልድ

ዛሬም ለበጎቻቸው ራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ እውነተኛ እረኞች አሉ።
በዛሬው የባህር ዳር ደመራ በዓል ላይ የተገኙት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ አብርሐም መጀመሪያ ሕዝቡ ወደቤቱ ሳይገባ እኔ አልንቀሳቀስም በማለት እዚያው ከቀሩ በኋላ በመጨረሻ በፖሊስ መኪኖች ታጅበው በዚህ መልክ በእግራቸው ወደ ባዕታቸው አምርተዋል።
አቡነ አብርሐም በደመራ በዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር ፦”ሕዝብ መቼም የችግር መንስዔ ሆኖ አያውቅም ። ቤተ ክርስቲያንም እንደዛው። ሁሌም የችግር መንስኤ የሀገሪቱ መሪዎች ናቸው ።መንግስት ለህዝብ ጩኸት መልስ አይሠጥም… መንግስት አዎንታዊ መፍትሄ እስካልሠጠ ድረስ ደግሞ ህዝብ ጩኸቱን አያቆምም.። እና የጥይት ምላጭ ከምትስቡ የፍቅር ምላስ ሳቡ” ብለዋል።
አቡነ አብርሐም አክለውም፦”..እናንተ ጋዜጠኞች ደግሞ ሁሌም ቃለመጠይቅ ታደርጉልናላችሁ፤ መርጣችሁ ምታስተላልፉ ግን እኛን ከህዝቡ ጋር የሚያጋጭ ነገር ነው። ህዝቡ “አባት የለንም” ብሎ እንዲያስብ ክውሆነ የምትፈልጉት ወደፊት እንድትቀርፁን ምንፈቅድላችሁ አይመስለኝም ። ለዛሬ ግን ችግር የለውም ነፃ ናችሁ።” በማለት የመንግስትና የድርጅት ጋዜጠኞችን ነቅፈዋል።
(እንዲህ ነው መንፈሳዊ አባት-ሥጋን ከሚገድሉ ምድራዊ ገዥዎች ይልቅ ሥጋንም፣ ነፍስም መግደል የሚችለውን ሰማያዊ አምላክ የሚፈራ።)
ረዥም ዕድሜና ጤና ለአቡነ አብርሐም!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *