ይሄን ለአዲስአበቤው አድርሱልኝ። አደራ። ፨፨፨

ይሄን ለአዲስአበቤው አድርሱልኝ። አደራ።
፨፨፨
#EthiopiaProtest “ትንሿ ኢትዮጲያ” አዲስ አበባ/ፊንፊኔ/ሸገር ከወገኖቻ ጋር ነች። መስቀልን ሁላችንም በየቤታችን ለእኛ ሲሉ በህወሀት ወያኔ የተገደሉ እና እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖቻችንን በፆም፣ በፀሎት እና ሻማ በማብራት አስበናቸው እንውላለን። የትግል ጥሪው ለሁሉም እምነት ተከታዮች ነው የቀረበው። ከትግራይ በላይ የስረዐቱ ቡችሎች ከተማችን ውስጥ ስላሉ እነዚህን የእምቢተኝነት አማራጮች ወስደናል።
፨፨፨
፩. የደመራ በዐልን ቤተክርስቲያናችንን ካቆሸሻት የስረዐቱ ካድሬ ቄሶች ጋር አናከብርም በመሆኑም በየሰፈራችን ችቧችንን አብርተን የጌታችንን ስም ጠርተን እና አወድሰን እናሳልፈዋለን።
፨፨፨
፪. አስራት ተብሎ ነገር ፈፅሞ አይታሰብም።
፨፨፨
፫. የመስቀልን እለት ከጥዋቱ 12 ሰዐት እስከ ምሽቱ 12 ስዐት ፆም ነው። በየማጎሪያው ያሉ ወገኖቻችን ረሀብ ምን እንደሚመስል በጨረፈታ እንዲሰማን። የሌላቸው ወገኖቻችን ፃም ማስፈታት እንዳይረሳ።
፨፨፨
፬. የመስቀልን እለት ሁላችንም በቤታችን ውስጥ እናሳልፈዋለን። በአንድ ክፍል ውስጥ በብዛት ታጉሮና ተወስኖ መዋል ምን እንደሚመስል በጣም በጥቂቱ እንድንረዳው።
፨፨፨
፭. ምንም አይነት አገልግሎት ከተማችን ውስጥ እንዲሰጥ አንፈልግም። በየሰፈራችን የሚገኙትን ሱቆች ጨምሮ። ለዚህም ቅድመዝግጅት ይደረግ።
፨፨፨
፮. ሁለቱንም ቀኖች በፀሎት እና ሻማ በማብራት እናሳልፋቸዋለን።
፨፨፨
የሸገር ልጆች ትናንትናም፣ ዛሬም ነገም ሰሜን ሆነ ደቡብ፤ ምስራቅ ሆነ ምእራብ ኢትዮጲያዊያን ወገኖቹ ሲነኩበት ያመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *