የመሬት ስርቆት ሱስ ???

የመሬት ስርቆት ሱስ?!

*መንግሥት ለ10 ዓመታት በመማሪያ መጻሕፍት ላይ የአማራ ክልልን መሬት በካርታ ላይ ወደ ትግራይ፣ ራስ ደጀን ተራራን በትግራይ የሚገኝ አድርጎ በማተም ትውልድን አስተምሯል።

*ትምህርት ሚኒስቴር “በስህተት ነው፣ ይቅርታ” ብሏል። ነገርግን ካርታው ከህወሓት ምጽአት ጋር አብሮ አዲስ አበባ የገባ፣ በሽግግር መንግሥት ምርጫ ኮሚሽን ጭምር ስራ ላይ የዋለ ነበር። በወቅቱ የተወካዮች ምክር ቤት በስብሰባ ላይ አንስቶ ተወያይቶበት “የውጭ ሀገር ሰዎች እንዲረዱት ነው” ተብሎ እንደሚወገድ ተነግሯል።

*የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት የላሊበላን ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት በትግራይ እንደሚገኝ ማስታወቂያ ሰርቷል። የብዙ ሰዎች ትችት ሲደርስበት Lalibela in Tigray ሳይሆን Lalibela and Tigray ነው የሚለው፣ ድምጹ አንሶ ስለተነበበ ነው የሚል ማስተባበያ በማውጣት እንደሚስተካከል ገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *