አማራውን ትጥቅ ለማስፈታት ወደ ወገራ ወረዳ የሄደው የትግራይ ነጻ አውጪ ጦር አፍረትን ተከናነበ

አማራውን ትጥቅ ለማስፈታት ወደ ወገራ ወረዳ የሄደው የትግራይ ነጻ አውጪ ጦር አፍረትን ተከናነበ September 15, 2016 | by: Zehabesha

(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት አስተዳደሮች አባይ ጸሓዬ; ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እና አባይ ወልዱ በተደጋጋሚ በየሚዲያው ወጥተው አማራውን ትጥቅ እናስፈታለን በሚል የፎከሩትን ፉከራ ለማሳካት በጎንደር እንቅስቃሴ ቢጀምሩም ዛሬም ለሁለተኛ ጊዜ ውርደትን እንደተከናነቡ ከስፍራው የመጡ መረጃዎች ጠቆሙ::
በጎንደር ወረዳደርጋጅ ቀበሌ ታግራ ጎጥ ገበሬዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የሄደው ከ25 የማያንስ የትግራይ ነጻ አውጪ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ተደምሥሷል:: የአማራ ገበሬዎች መሣሪያችንን አናስረክብም በሚል ከትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት ጋር እልህ አስጨራሽ ተኩስ መክፈታቸውንም የክስፍራው የደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል::

እንደሌሎች የመረጃ ምንጮች ገለጻ የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት በአማራው ክልል ውርደትን ሲከናነብ ይህ የመጀመሪያው አይደለም:: ከጥቂት ቀናት በፊት በሰሜን ጎንደር ወገራ ወረዳ ታግራ መድሃኔዓለም ቀበሌ ገበሬውን ትጥቅ አስፈታለው ብሎ የተንቀሳቀሰው ቁጥሩ በይፋ ያልታወቀው የሕወሓት ሰራዊት በገበሬዎች ተደምስሷል::

በአማራው ክልል ያሉ ገበሬዎች አሁንም ትጥቃችንን አንፈታም በሚል ከትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት ጋር በተለያዩ ቦታዎች እየተዋደቁ ቢሆን በኢንተርኔትና በስልክ እጦት የተነሳ መረጃዎች ሕዝብ ጋር በቶሎ ሳይደርሱ ቀርተዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *