ወያኔ የማወጣው እልቂት ውስጥ ሳይገባ ከኢትዮጵያ እራስ ላይ ይውረድ !!!

መንግስት ያለውን ብሏል ። እኛ ደሞ «ዲሞክራሲን የመከነ ልማት መጨረሻው አንበጣ የበላው የማሽላ አገዳ የሚመስሉ ፎቆች ባለቤት መሆን ነው።» እንላለን ። የተገነቡ ፎቆች መሰረታቸው አርማታ ሳይሆን የህዝብ ነፃነት ካልሆነ ፥ መፍረሳቸው አይቀርም ። ቁመታቸው የዜጎችን እኩልነት የሚያሳይ ካልሆነ ፥ መደርመሳቸው አይቀርም ፥ ሽንጦቻቸውን የዘረጉት አንገቱን በደፋ ህዝብ መሃከል ከሆነ ከፎቅነት ይልቅ ወደሰማይ የተንፏቁቁ ድንጋዮች ናቸው ። ሰማይ ጠቅሰው ባለም የሚያስጠሩን እና የሚጠሩ ሳይሆኑ እንደባቢሎን ተንጠልጥለው የሚቀሩ የድንጋይ እርካቦች ናቸው። ከነፃነት በፊት ልማት ሲቀድም ፥ በነፀነት ጥያቄ የለማው ወደ ዶጋ አመድነት ይቀየራል ። የተሰሩት ፎቆች እንዳይፈርሱ ስንል ፥ ሰዋዊ ክብራችንን አፍርሰን መኖር ተፈጥሯዊ ማንነታችን አይደለም ። ከሰሜን እስከ ምስራቅ የተለጠጡት አውራ ጎዳናዎች በሰላም ውለው እንዲያድሩ ፥ ነፃነቱን ያጣ ህዝብ ደሙንም ቢሆን ገብሮ አርፎ መቀመጥ አለበት የሚል አመለካከት የሚሰራው ፥ ከስጋ ና ከደም ለተሰራ ሰው ሳይሆን ፥ ህብለ ሰረሰሩ ባርማታ እና በብረት ለቆመ ፥ ባሸዋ እና በሲሚንቶ ለሚተነፍስ ግዑዝ አካል እንጂ ለሰው ልጅ አይደለም ። በባርነት ከሚያማምሩ ፎችቆች መሃል ከመቆም ፥ በነፃነት ከፍርስራሾቹ ውስጥ አካላችን ተጎትቶ ቢወጣ እንመርጣለን ። ሰው የሚያስብለን እሱ ነውና ! ፎቅ እንዳይፈርስ ብለን እንገታችንን ደፍተን እንድንኖር እትጠይቁን ! እናደርገውም !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *