ተአምረኛው ብላቴና!!!!

ተአምረኛው ብላቴና
ለገሠ ወ/ሃና
ትላንትና የመኢአድ አመራርና አባላት ላይ ወያኔ እያደረሰ ያለውን ማሳደድ የተመለከተ አጭር መልክት ለጥፌ ነበር ግን መካተት የነበረበት ያልተካተተ ነገር ዘግይቶ ስለደረሰኝና እጅግ በጣም ጠቃሚ ስለሆነ ሁሉም ጥንቃቄ እንዲያደርግ ለማሳሰብ ይህንን መልክት በድጋሚ ለጥፌለሁ
ህወሃት ከመቼውም ጊዜ የበለጠ በመላ ሀገሪቱ በተለይም በአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት ማወጁ ይታወቃል ይህንን ተከትሎ በግልፅም በስውርም ደህንነቶችን አሰማርቷል አሁን ደግሞ የአእምሮ ህመምተኛ የሚመስሉ ነፍሰ ገዳዮችን አስታጥቆ አሰማርቷል ለዚህም ማሳያ የሚሆነን በታላንትናው ዕለት ህጋዊ የመኢአድ ም/ል ፕሬዝደንት የሆነውን ዘመነ ምህረት ለመግደል በህወሓት የተላከችው የአእምሮ ታማሚ በመምሰል ስትንቀሳቀስ በቤተሰቡና በአካባቢው ወጣቶች በተደረገው ክትትል ከሽፏል ይችው የህወሓት ገዳይ በሰጠችው ቃል መሠረት ዘመነ ምህረትን ለመግደል እንደተላከችና እሱን ማግኘት ካልቻለች ልጁን አንድነት ዘመነን በመያዝ ዘመነ ለልጁ ሲል በነሱ እጅ እንዲገባ ተልዕኮ ተሰጥቷት እንደነበረ ተናገግራለች በጣም የሚያስደንቀው የአእምሮ ታማሚ መስላ በነዘመነ መኖሪያ ቤት አካባቢ ስትንቀሳቀስ የነበረችውን ደህንነት መጀመሪያ የተመለከታት አንድነት ዘመነ ነው ይች ሴትዮ በተደጋጋሚ ወደ እኔ ታያለች ሰላም ትለኛለች ብሎ ለቤተሰቡ ጥቆማ በመስጠቱ የተጠራጠሩት ወጣቶች ፍተሻ ሲያደርጉባት አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም የሚል ደብተር ላይ የዘመነ ምህረት ፎቶግራፍ ተለጥፎ ተስጥቷት ይዛው ተገኝታለች እንዲሁም ሽጉጥና በርከታ መታወቂያ አግኝተውባታል በአጠቃላይ በጎንደር ክፍለ ሀገር ብቻ ልክ እንደ እሷ አይነት 300 ደህንነቶች የአእምሮ ታማሚ በመምሰል በተመረጡ ሰዎች ላይ ግድያ እንዲፈፅሙ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው መበተነቸውንም ነግራቸዋለች ከዚህ የምንማረው በርከታ ቁብ ነገር አለ ይኸውም በመላ ሀገሪቱ የምትገኙ በግልፅ አገዛዙን ስትቃወሙ የነበራችሁ ወገኖችን ተገቢውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ አሳስባለሁ
በጠም አስገራሚው ነገር የዚችን ገዳይ ማንነት የታወቀው በትንሹ ብላቴና በብልሁ አንድነት ዘመነ ነው አንድነት በጣም አስተዋይና ጥበበኛ ልጅ ነው የሚያያቸውን ነገሮች እንደ ልጅ ዝም ብሎ አያልፍም የሚያየው እንግዳ ነገር ለታላላቆቹ ያሳውቃል ይህ ብልህና አስተዋይ ብላቴና የተመለከተውን እንግዳ ክስተት በማሳወቁ የራሱን እና የአባቱን ህይወት አትርፏል
አንድነት ዘመነ መስከረም 5 2009 ዓም 5 ዓመት ይሞላዋል የሚገርመው ባለፈው አመት አባቱ እስር ቤት ሆኖ ነበር ልደቱ የተከበረለት ዘንድሮ ደግሞ ጭራሽ ከባለፈው በባሰ ሁኔታ ከእናቱ ጋር ቤታቸውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታ ለመሰደድ ተገደዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *