ብአዴን የአማራን መሳሪያውን በአጋዚ አስገዳጅነት እየስፈታ ነው !

#AmharaResistance;
ሰበር ዜና፤ በጎንደር መሣሪያ መግፈፍ ዛሬ ተጀምሯል
ዛሬ ጳጉሜ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. በጠዋት የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ በማቋረጥ የትግራይ ወታደሮች የዐማራውን ሕዝብ መሣሪያ እየነጠቁ ነው፡፡ መሣሪያ መግፈፍ የተጀመረው በጎንደር ከተማ ሲሆን ከአየር ማረፊያ ጀምሮ ወታደሮች ቤት ለቤት እየዞሮ በመፈተሸ የዐማራውን ሕዝብ መሣሪያ እየነጠቁ ነው ተብሏል፡፡ ከጠዋቱ 1፡00 ጀምሮ ይህ ዜና እስቀተጠናቀረበት ሰአት ድረስ ማንኛውም የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎትም እንደተቋረጠ ለማወቅ ተችሏላል፡፡
መረጃውን ያቀበሉን ሰዎች የመሣሪያ መቀማቱ ሥራ ወደ ገጠሩ የዐማራው አካባቢም ሊከናወን ስለሚችል ገበሬው በተጠንቀቅ እንዲቆም መልእክት መተላለፍ ይኖርበታል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
(ማሳሰቢያ፤ ይህን መረጃ የምታነቡ ሰዎች ለዘመድ ወዳጆቻችሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ታሳውቁ ዘንድ እንጠይቃለን)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *