ወያኔ ለኢትዮጵያ ህዝብ እኔ ከሌለው ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የለም ይሉናል የትግራይ ኤንባሲ አንባሳደር ስም የለሽ !

አምባሳደር??? ያሳፍራል። እውቀት የሚጠይቅ: ልምድ ግድ የሚለው: በዓለም አቀፍ ደረጃ ስታንዳርድ ያለው ክቡር ሃላፊነት ነው። የሀገር ምልክት ነው። መታወቂያ ነው። ህወሀት ዘንድ ደርሶ ረከሰ እንጂ። ስንቱ ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶች እንዳልተቀመጡበት: ከሀገር አልፈው አህጉር እንዳላስጠሩበት ህወሀት መጣና የማንም አቅመ ደካማ መጫወቻ አደረገው። ጥይት ተኩሶ ትውልድ ከመግደል ያልተናነሰ በሀገር ላይ የሚፈጸም ወንጀል ማለት ከዚህ በላይ የለም። ስትናገር እንደ ቢንቢ ጆሮ ላይ የምትጮህ: ከእውቀት የጸዳች መንደርተኛ ሴት የሀገር አምባሳደር አድርጎ ከማስቀመጥ በላይ ምን ወንጀል ይኖራል? አዳምጬ መጨረስ አቃተኝ። ያጥወለውላል። ደሟ ተንተክትኮ የምትረጫቸው ሰቅጣጭ ቃላት ከድምጿ ማቃጨል ጋር ከጆሮ ሲደርስ የሆሊውድ ሆረር ፊልም ላይ የሚሰማው አስፈሪ ሳውንድ ትራክ ይመስላል። ኡፍፍፍፍ ያቺን ደቂቃ ላዳመጥኳት ነፍሴ ተጨነቀች። …..አምባሳደር?!

የማያውቅ ሰው ደፋር ነው። እወቀትና ልምድ ሲያጥርህ ትዕቢትና እብሪት ይቆጣጠሩሃል። ስለተናገረችው አስተያየትም መስጠት አያስፈልግም። ውሸት የነፍስህ ምግብ ነው። ይሉኝታን ቅርጥፍ አድርገህ ትበላና አይንህን በጨው አጥበህ ሰው ፊት ትቀርባለህ። ማይክ ይሰጡሃል። ትጮሃለህ። …..ትርፉ ትጮሃለች። እንደቢንቢ የሚሰቀጥጥ ድምጽ ታወጣለች። ድንገት ፍሬን እንደያዘ መኪና… ሲ.ጥ.ጥ.ጥ.ጥ.ጥ ምቾት ይነሳል። ….ወይ ‘አምባሳደር’!!!
ካሳሁን ሰቦቃ ግን ምን ነካው? ከመሳይ መኮንን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *