በድንጋጤ የሞተው የደቡብ ወሎው ባንዳ ባለሥልጣን ቦታው በደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ ነው!

በድንጋጤ የሞተው የደቡብ ወሎው ባንዳ ባለሥልጣን
ቦታው በደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ ነው፡፡ ይህ ቅጥረኛ ባንዳ አቶ ልዑልሰገድ በቀለ ይባላል፤ የደቡብ ወሎ ዞን የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት መምሪያ ኃላፊ ነበር፡፡ የዐማራው ተጋድሎ በመላው ዐማራ ሕዝብ ሲቀጣጠል የመካነ ሰላምን ዐማራ ያሳምናል ተብሎ ከዞን ተላከ፡፡
ነሃሴ 6 ቀን 2008 ዓ.ም. በመካነ ሰላም ከተማ የመንግሥት ሠራተኞችንና ካቢኔዎችን ሰበሰበ፡፡ ከወልቃይት ጠገዴ የዐማራ የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ገለጻ ሲያደርግ የግብር አባቱን የወያኔን ሀሳብ ተናገረ፡፡ በስብሰባው የነበረው ሕዝብ በአንድነት ጮኸበት፡፡ በድንጋጤ ክው አለ፤ የሕዝቡን ድምጽ ፈርቶ ወደ ኋላ ወንበሩን ለማንቀሳቀስ ሲሞክር ወንበሩ ተገለበጠ፡፡ አቶ ልዑልሰገደም ከግዑዙ ወንበር ጋር አብሮ ወደ ኋላ ወደቀ፡፡
ሕዝቡ አሁንም በንቀት ሳቀበት፤ እርሱ ግን ከወደቀበት ሊነሳ አልቻለም፡፡ የመካነ ሰላምን ዐማራ አሳምናለሁ ያለው ባንዳ በበደንጋጤ በተፈጠረ ምራቅ ትንታ መካነ ሰላም ሆስፒታል ገባ፡፡ ትንታው ሊስተካልለት ባለመቻሉ ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ተወሰደ፡፡ በዚያው ቀን ከቀኑ በ9፡00 ሞተ፡፡ የባንዳ ታሪክ ይህ ነው፤ ዐማራው እንኳን ተነስቶ ድምጹም እንዲህ በድንጋጤ ያርዳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *