በቅሊንጦ እስር ቤት ወያኔ እሳት ለኩሶ በአሰቃቂ ሆኔታ እስረኛወቹንፈጃቸው!!!!!

(አሳዛኝ ዜና) ጳውሎስ ሆስፒታል፣ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል እና ፖሊስ ሆስፒታሎች ከቂልንጦ እስር ቤት በመጡ 49 አስከሬኖች ተጨናንቀዋል ተባለ

(ይህን ዜና ስጽፈው እጄ እየተንቀጠቀና እምባዬ እየወረደ እንደሆነ ይታወቅልኝ )

በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ትናንት የተነሳውን ቃጠሎ ተከትሎ የመንግስት ወታደሮች እስረኞች ሊያመልጡ ነበር በሚል በመተኮስ የገደሏቸው እስረኞች ቁጥር እያሻቀበ ነው::
ከአዲስ አበባ የመጡ የታማኝ ምንጮች ዘገባ እንደሚያመለክተው ጦር ኃይሎች ሆስፒታል፣ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል እና ፖሊስ ሆስፒታሎች በአስከሬኖች ተጨናንቀዋል::

እንደዘገባዎች ከሆነ በአጠቃላይ ትናንት የተገደሉት እስረኞች ቁጥር ወደ 49 አሻቅቧል:: በጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አሉ የተባሉ አስከሬኖች ቁጥር እስካሁን ያልታወቀ በመሆኑ ቁጥሩ ከ49 በላይም እንደሚያድግ የሚገልጹት ምንጮች በጦር ኃይሎች ሆስፒታል 13 የ አስከሬኖች; በጳውሎስ ሆስፒታል 22 እንዲሁም በፖሊስ ሆስፒታል 14 እስረኞች አስከሬን እንዳለ ገልጸዋል:: የ ሟቾች ቁጥር እስካሁን አልታወቀም:: ብዙ ቤተሰብ ተጨንቆ ወደ ቅሊንጦ ቢያመራም እስረኞችን ማየት እንደማይችሉ ተገልጾላቸው ተመልሰው ነበር:: ሌሎች እስረኞች ዛሬ ሌሊት በ20 መኪኖች ተጭነው ወደ አልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸው አይዘነጋም:: ከ ethio-sunshine

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *