የመጨረሻው የወያኔ ዘመን የመቀበሪያውን ጉድጋድ ቆሞ እያየው ነው !

የህወሀት ኋላቀር ስትራቴጂ
ቤተመንግስት ርዷል። ወንበሩ ነቅነቅ ማለት ጀምሯል። ለውጥ ከ4ኪሎ ደጃፍ ቆማለች። አንድ እግር ሀገር ቤት አንድ እግር ባህር ማዶ ያደረጉ የህወሀት ሰዎች የለውጡ አይቀሬነትን እያቃራቸውም ቢሆን ይናገራሉ። ግን ደግሞ ተስፋ አይቆርጡም። ድንገት የተነሳውን ማዕበል፡ አጣልተን፡ አናክሰን፡ አቧጭቀን፡ ጥገናዊ ለውጥ አድርገን፡ ጥቂት ባለስልጣናትን አባረን የምንቀለብሰው ከሆነ ብለው መፍጨርጨራቸው አይቀርም። ለዚህም መናጆ የሚሆኑ ባለስልጣናት ተዘጋጅተዋል። የፌስ ቡክ ሰራዊታቸው ቀድመው መረጃ እንዲያሾሉኩ አድርገው የልብ ትርታ ይለካሉ። ከዚያም እከሌ የሚባል የእንትን ሚኒስትር ተባረረ። ታሰረ። ተገረፈ ምናምን የሚሉ ወሬዎችን በመልቀቅ ማደንቆር ይጀምራሉ። በሞት አፋፍ ላይም የመኖር ተስፋ አይጠፋም የምትለዋን አባባል ሰንቀው የኢትዮጵያን ህዝብ ላለፉት 25 ዓመታት እንዳላገጡበት አሁንም ሊያላግጡ ይሞክራሉ።

ግን የእነሱ ጀምበር እየጠለቀች መሆኗን በወሬ ሳይሆን በተግባር ህዝብ እያሳያቸው ነው። ሽርፍራፊ ተስፋ የለም። ኋላ ቀር የድንቁርና መገለጪያችሁ ዘንድሮም ይሳካልናል ብላችሁ አትሞኙ። የቤት እንስሳችሁን እንኳን ለማሳመን የሚያስችል ስብዕናና ሞራል የላችሁም። ለውጡ የባለስልጣናት ሽረት አይደለም። የስርዓት ለውጥ እንጂ። የእናንተን ውድቀትን የሚያበስረው ለውጥ!!!!!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *