ከወሎ ህዝባዊ እንቢተኝነት አስተባባሪ ግብረሃይል የተላለፈ መግለጫ

ሰበር ዜና

ከወሎ ህዝባዊ እንቢተኝነት አስተባባሪ ግብረሃይል የተላለፈ መግለጫ !!
ከዚህ በታች ስማቸው የተጠቀሱት የአማራ ክልል ከተሞች የገጠር ቀበሌዎችና ገበሬ ማህበራት ነዋሪዎች በሙሉ። እንደሚታወቀው በጎንደር እና በጎጃም ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ህዝባዊ እንቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴው ህዝቡ አሁን ከደረሰበት ራሱን ነጻ ማውጣት እንቅስቃሴ በተፈለገዉ ፍጥነት የዕንቢተኝነት እንቅስቃሴዎችን እየመራዉ ይገኛል። ይሁንና አፋኙና ገዳዪ መንግስት በተለይ በወልድያ ደሴ ኮምቦልቻ ከሚሴ ሸዋሮቢት ደብረሲና ደብረብርሃን ከተሞች ገዳዩና አፋኙ ህውሃት መተናፈሻ ከተሞች በመሆናቸው ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቁጥር አግአዚ ወታደሮች በማስገባት ቀላል የማይባል ቁጥር ህዝብ በማፈን ወደማይታወቅ ቦታ መውሰዱን ነዋሪው ራሱ ምስክር ነው። እስከዛሬም ዕለት ይኸው አፈና ቀጥሏል። ይሁንና የጎንደርና የጎጃም ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት የእኛው ጉዳት እንደሆነ ቆጥረን የህዝባዊ እንቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ አስቸኳይ መግለጫ ሰጥቷል።
በወልድያ ደሴ ኮምቦልቻ ከሚሴ ሸዋሮቢት ደብረሲና ደብረብርሃን ከተሞችና አካባቢዎች ላይ
ከእሁድ 29/12/2008ዓ ም ጀምሮ እስከ ጷግሜ 2/2008 ዓም ድረስ የሚቆይ ከቤት ያለመወጣት አድማ ታውጇል።

በተጠቀሱት ከተሞች ላይ ይህንን አድማ ተግባራዊ የማያደርግ ማንኛውም ግለሰብ በጎንደርና በጎጃም በህውሃት ጥይት የፈሰሰውን የወገኖቻችንን ደም እንደመርገጥ ስለሚቆጠር ግብረሃይሉ ከመድኃኒት ቤቶች በስተቀር ማንኛውም ዓይነት ንግድ ቤቶችን ጨምሮ አውቶቡስ ሚኒባስ ባጃጆች ሌሎችም እንቅስቃሴዎችን ሲገኝ ግብረሃይሉ በሚወስደው እርምጃ ማንም ኃላፊነት የሌለው መሆኑን ይገልጻል።
-…ግብረኃይሉ …-

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *