በጎንደር አንገረብ እስር ቤት የሚገኙትን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴን ለመያዝ የሲቪል ልበስ ለብሰው የገቡ የደህንነት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጎንደር አንገረብ እስር ቤት የሚገኙትን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴን ለመያዝ የሲቪል ልበስ ለብሰው የገቡ የደህንነት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ነሃሴ ፲፰ ( አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-

የደህንነት አባላቱ አንዴ ታዘን ነው ሌላ ጊዜ ደሞዝ ልንከፈል ነው የመጣነው ቢሉም ፣ የዞኑ ልዩ ሃይልና መከላከያ ሰዎች የምናውቀው ነገር የለም በማለት እነዚህን ሰዎች ማገታቸው ታውቋል። ሁሉም የደህንነት አባላት ሽጉጥና ሌሎችንም የጦር መሳሪያዎችን መያዛቸው ታውቋል።

በአሁኑ ሰአት እስር ቤቱ አካባቢ ከፍተኛ ውጥረት እንደሚታይ ምንጮች አክለው ገልጸዋል። ኮ/ል ደመቀ ዘውዴን ከጎንደር ከተማ አውጥቶ ለመውሰድ ተደጋጋሚ ሙከራዎች ሲደረጉ ቢቆዩም አልተሳኩም። የአሁኑ ድርጊትም የከተማውን ህዝብ ማስቆጣቱ ታውቋል። ህዝቡ በቤቱ ቁጭ ብሎ አድማ እያደረገ ባለበት ሰአት ኮሎኔሉን ለመውሰድ የተደረገው ሙከራ በደንብ የታሰበበት ሊሆን እንደሚችል ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *