የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በኢትዮጵያ የሚገኙ ዜጎቹ እንዲጠነቀቁ አሳሰበ!

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በኢትዮጵያ የሚገኙ ዜጎቹ እንዲጠነቀቁ አሳሰበ
#USA #StateDepartment #Ethiopia #TravelAlert

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክልሎች መንግሥትን በመቃወም በሚካሄዱት አንዳንድ ግጭት የታከለባቸው ተቃውሞዎች ምክንያት አደጋ ሊኖር እንደሚችል በመግለጽ ለዜጎቹ ማስጠንቀቅያ አውጥቷል።የስልክና የኢንተርነት አገልግሎት መቆራረጥ በኢትዮጵያ ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ በሀገሪቱ ካሉት የአሜሪካ ዜጎች ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት እንዳሰናከለበት መግለጫው ጠቅሷል። ይህ ማስጠንቀቅያ እስከ የካቲት 2017 ዓ. ም እንደሚዘልቅ የማስጠንቀቂያ መግለጫው ይጠቁማል ።የተቃውሞ ሰልፎቹ ካለፈው ዓመት ሕዳር ወር ጀምሮ በተለይም በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በተቃዋሚዎች መካከል ግጭት እንዳስከተሉ መግለጫው ጠቅሶ፤ ተቃውሞዎቹ ሊቀጥሉና ሊስፋፉ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳለ አስፍሯል። በዚህም ምክኒያት በኢትዮጵያ የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፣ ደህንነታቸውን እንዲጠብቁና የተቃውሞ ሰልፎችንና ሰዎች በብዛት የተሰባሰቡባቸው ቦታዎችን እንዲያስወግዱ አሳስቧል።
http://amharic.voanews.com/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *