መሰለ ገ/ሕይወት ሆቴል ሳይከፍት አስመጪና ላኪ ሳይሆን የህዝብ ገንዘብ ተጠቅሞ ሚሊየነር የሆነ ማንም የማያውቀው ድብቅ ባለሐብት ነው።

ድብቅ የህወሀት ባለሀብቶች

ብዙዎቻችን ስለህወሀት አመራሮች ስናወራ የኢትዮጵያን ህዝብ ገንዘብ የሚዘርፉት የበላይ አመራሮቹ ብቻ ይመስሉናል ሆኖም ተራ የህወሀት አባላት እንኳን በዚህ ብልሹ ፖለቲካዊ ድርጅት የተነሳ መልቲ ሚሊየነር ሆነዋል ከእነዚህም ውስጥ አንዱ በኢቲቪ ዜና ሲያነብ የምናውቀው መሰለ ገ/ሕይወት አንዱ ነው።
መሰለ ገ/ሕይወት ሆቴል ሳይከፍት አስመጪና ላኪ ሳይሆን የህዝብ ገንዘብ ተጠቅሞ ሚሊየነር የሆነ ማንም የማያውቀው ድብቅ ባለሐብት ነው።
በኢትዮጵያ በሚገኙ ሁሉም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ለመልካም ገፅታ ግንባታ በሚል የሚበጅቱት በጀት አለ ይህ የበጀት አይነት ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ የሰራቸውን መልካም ስራ ለሕዝብ እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያሳይና ሁሉም ህዝብ ለመስሪያ ቤቱ መልካም የሆነ እይታ እንዲኖረው በማሰብ የሚበጀት በጀት ነው። ይህ በጀት እንደየመስሪያ ቤቶቹ ሁኔታ እስከ አምስት ሚሊየን ብር ይደርሳል ይህንን በጀት ነው መሰለ ገብረሕይወት ከየሚኒስትር መስሪያ ቤቱ እየሰበሰበ ሚሊየነር የሆነው።
መሰለ ገብረሕይወት ይህንን ገንዘብ ለማግኘት እንዲረዳው “ሽግግር” የተሰኘ መፅሔት አለው በዚህ መጽሔት ላይ የመስሪያ ቤቶቹን ስም እና የኢህአዴግ ሹማምንትን ስም ከፍ አድርጎ በማንሳት የመልካም ገጽታ በጀቱን ወደኪሱ ይከታል።
በዚህ ሽግግር በተሰኘች የመሠለ ገብረሕይወት መጽሔት ላይ ስሙ በወርቅ ያልተፃፈ የኢህአዴግ ሚኒስትር የለም ከቴዎድሮስ አድሐኖም እስከ ደመቀ መኮንን ከአባተ ስጦታው እስከ ኩማ ደመቅሳ ስማቸውና መሥሪያ ቤታቸው በሙገሳ ተፅፎላቸው ለመሰለ ገብረሕይወት በሚሊዮን የሚቆጠር የህዝብ ገንዘብ ሰጥተውታል።
ለምሳሌ ከዛሬ አምስት አመት በፊት “ኢትዮጵያን የአፍሪካ የትምህርትና የምርምር ማእከል ያደረጉ ታላቅ መሪና መሥሪያ ቤታቸው” የተሰኘ ፅሁፍ ፅፎ ከትምህርት ሚኒስትር አንድ ነጥብ ሦስት ሚሊየን ብር ወስዷል።በዚሁ ፅሁፉ ደመቀ መኮንን በመምህርነት ዘመኑ አንቱ የተባለ በተማሪዎች የተወደደ እንደነበረ ያትታል ሆኖም ደመቀ መኮንን በአቅም ማነስ ከባዮሎጂ መምህርነት ተነስቶ ስፓርት አስተማሪ መደረጉን በወቅቱ አብረውት ይሰሩ የነበሩ መምህር አሁንም በእስር ላይ የሚገኘው ተመስገን ደሳለኝ በሚያሳትማት ፍትህ ጋዜጣ ላይ መናገራቸውን እናስታውሳለን ሆኖም ሰውዬው መሰለ ገብረሕይወት አላማው ገንዘብ መሰብሰብ ነውና እንደደመቀ መኮንን ያሉ የኢህአዴግ ባለሥልጣናትን ስም አጉልቶ ሲፅፍ ልባቸው ሀሴት አድርጋ በደስታ እየፈነደቁ ለመልካም ገፅታ የያዙትን በጀት እየመዠረጡ ይሰጡታል እርሱም በህዝብ ገንዘብ ዛሬ የናጠጠ ሚሊየነር ሆኗል።
በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲህ የሚል አንድ ስንኝ መቋጠር ፈለግኩ
.
“ዋሾ ከወደደ ሀገሬው በሙላ
ውሸትን ቸርችረህ እንጀራህን ብላ”
#ኤርሚያስ_ቶኩማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *