በጥንቃቄ አማራ መጨረስ ይሉሀል እንዲህ ነው !

መረጃውን እንደወረደ ስናቀርበው ይህንን ይመስላል ( እጅግ ከታመኑ ምንጮች ወይም ከፈረሱ አፍ የሚሉት ነው )

ልጅ ሄኖክ
ዘወትር የምትሳሳለት የአማራው ሕዝብ ምን እንደፈረደበት ብነግርህ ያምሃል። ግን መታወቅ ስላለበት ነው። ሕዝባዊ ተቃውሞው በጀመረ ማግስት በጎንደር፣ በባህር ዳር፣ በደ/ማርቆስ፣ እንዲሁም በ24 ተቃውሞ በተነሳባቸው ሌሎች ወረዳዎች ላይ የአተት በሽታ ተከስቷል። የበሽታው ምንጭ በእርግጠኝነት መንግስት ይሁን አይሁን መናገር ባይቻልም ከሁነቶች ግጥምጥሞሽ ተነስተን መጠርጠር ግን ይቻላል።

አሁን ልነግርህ የምፈልገው ጉዳይ ባህር ዳር አባይ ማዶ (አዲስ አለም) ሆስፒታል ብቻ ከ500 በላይ በሽተኞች በድንኳን ይገኛሉ። ለህክምናውም አንድ ሰው ቢያንስ ከስድስት በላይ የታሸገ ፈሳሽ(Normal Saline) ያስፈልገዋል። ይሁን እንጂ ዛሬ ጠዋት የሰማነው መርዶ ክልሉ 10,000 ብቻ የታሸገ ፈሳሽ እንዳለው ነው። ይህ ማለት ፈሳሹ እንኳንስ በሪፈራል ለሚመጡ በሽተኞች ይቅርና አሁን ገብተው ለሚታከሙት ራሱ በቂ አለመሆኑን ነው። በዚህም ጠዋት ላይ በነበረው የውይይት (Morning) ፕሮግራም ላይ ስፔሻሊስት ሐኪሞች የምር እንባ አውጥተው እያለቀሱ ነበር። ምርጫ የለም!!! የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ስለጉዳዩ ተነግሮት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥ ቢጠየቅም የሰጠው ምላሽ “አላውቅም፣ አያገባኝም” የሚል ነበር። እናም እልሃለሁ ማጣፊያው አጥሮናል። ከስደት ከረሃብ ከጥይት ብንተርፍም ደሞ ይኸው በበሽታ መጥተውብናል ። ያም ሆኖ መታገላችንን አናቆምም !

አመሰግናለሁ ወንድምህ !

እንደገባኝ ወያኔ በሽታውን ፈጠረ ። የመድሃኒት እጥረት ሆን ብሎ በመፍጠር ሰውን እርስ በእርሱ እንዲጋጭ ለማድረግ አሰበ ። መፍትሄው አዲስ አበባም ሆነ ሌላ ቦታ ያሉ የመድሃኒት ማከማቻዎችን መዝረፍ! እና ህዝብን ማዳን ነው !

ኄኖክ የሺጥላ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *