በተገኘ ውስጣዊ መረጃ የአማራ ክልል አስተዳደር በትግራይ ህወሓት እጅ ስር ወድቋል።

በባይነሳኝ ወልደማርያም
(ማምሻውን) በተገኘ ውስጣዊ መረጃ የአማራ ክልል አስተዳደር በትግራይ ህወሓት እጅ ስር ወድቋል። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከመደበኛ ስራቸው ተነስተዋል። የአማራ ክልል ምክርቤት በአስቸኳይ ስብሰባው ገዱ አንዳርጋቸውን በይፋ ከስልጣን ያነሳል ተብሎ ይጠበቃል።
የአማራ ክልል አስተዳደር በ5 ኮማንድ ፖስቶች ተዋቅሯል።
1.ምዕራብ ጎጃም ኮማንድ ፖስት
2.ምስራቅ ጎጃም ኮማንድ ፖስት
3.ጎንደር ኮማንድ ፖስት
4.ወሎ ኮማንድ ፖስት
5.ባህርዳር ኮማንድ ፖስት
ምስራቅ ጎጃም ኮማንድ ፖስት በዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል ከደብረማርቆስ ይመራል። ምዕራብ ጎጃም ኮማንድ ፖስት በብናልፍ አንዷለም፤ ወሎ ኮማንድ ፖስት በአለምነው መኮንንና ገነት ዘውዴ ጥምረት፤ ጎንደር ኮማንድ ፖስት በተፈራ ደርበውና አይለኝ ሙሏለም ይታዘዛሉ። ተጨማሪ ኮማንድ ፖስት ሰሜን ሽዋ ላይ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል።
ሁሉም ኮማንድ ፖስቶች በአንድ እዝ ስር ሆነው በደመቀ መኮነን እገዛ በአባይ ፀሃዬ ይመራሉ። የአማራ ክልል ፀጥታና ደህንነት ቢሮ መሉ በሙሉ በህወሓት ማዕከላዊ የፖለቲካ አመራር ስር እንዲሆን ተወስኗል። ምንጭ ዘሀበሻ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *