ድብቁ የበረከት ስምዖን ባለ 4 ኮከብ ሆቴል በባህር ዳር

ድብቁ የበረከት ስምዖን ባለ 4 ኮከብ ሆቴል በባህር ዳር

እንቅዩጳዝዩን_ባህርዳር
መላው የሀገራችን ከተማ ነዋሪ እያየ እያጉረመረመ እርስ በእርሱ እያወራ የሚነጋገርበት የደሀ ጥግ ላይ የነበረ ሰው ደርሶ ባለ ብዙ ፎቅ ቤት ሲሆን በመላ ሀገራችን እያየን እንገኛለን።የእውነታ ነገር ያቅራል ፥ቢመርም እንቅመሰው የሰማሁትን መረጃ ላካፍላችሁ ወደድኩ ፦ባህርዳር ቀበሌ 05 በተለምዶ ኮሸኮሽ (የሴት አዳሪ እህቶቻችን በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩበት ሰፈር ) ከድብ አንበሳ ሆቴል ጀርባ ማለት ነው ። አቶ አበበ ይመኑ ይባላል ይህ ሰው ቻግኒ ከተማ ከድሃ ቤተሰቦች ተወልዶ ያደገ ነው ።ከ10 አመት አካባቢ በፊት ከድብ አንበሳ በተኃላ ከሉት ክፍሎች ተከራይቶ አርኪቴክቸር ሙያ ይሰራ ነበር።የአቶ አበበ ይመኑ አሁን ያገባት ባለቤቱ በነበረከት ስምዖን የሚመራው የወያኔው ኢፈርት ተጓዳኙ የጉና ንግድ ስራወች ውስጥ ትሰራለች ።ይች ጋዜጠኛ ሙያ የምትሰራው ልጅ ለበረከት ስምዖን ወሲብ ማርኪያ ነበረች አሁንም ነች ። በረከት ስምዖን ሲያጠና አቶ አበበ ይመኑን ለሆድ ጥቅም ደለለውና ልጅትን ጋር ጀመሩ ።ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት ራህናይል ሆቴል በፍጥነት በሽፋን በአቶ አበበ ይመኑ ስም ተሰራ ዋና ንብረቱ የአቶ በረከት ስምዖን ነው። (ተመልከቱት የቤቱ በ ‘በ ‘ ቅርፅ ነው ዲዛይኑ ) በዚህ ሆቴል የመንግስት ትልልቅ ስብሰባወች ይደረጋሉ ብዙ የህዝብ ብር ይፈስበታል ይዘረፋል። አቶ አበበ ይመኑ አሁን ጤናቸው አሳሳቢ ላይ ይገኛል፤አዕምሮቸው እየለቀቀ መቀላቀል ጀምረዋል ።እውነት ያስለፈልፋልና “የኔ እኮ አይደለም የበረከት ነው ” እያሉ ሲናገሩ ይደመጣሉ ። የሚያውቅ ያውቀዋል ባህርዳር ላይ ትልልቅ የሚባሉት የድንጋይ ድርድሮች በአብዛኛው ስውር የወያኔ ወንበዴ አባላት እጅ እንዳለበት ይታወቃል ለምሳሌ ፖፒረስ ሆቴል (አቶ አዲሱ ለገሰ የሰውየውን ሚስት ነፍሱን ይማረውና እያማገጠ ሰውየውም አረፋ አሁን በበላይነት ይዞታል ) ግራንድ አዜብ መስፋን ትጠየቅ ወ/ሮ ትልቅ ሰው ገዳሙ በውሸት አለም እኛን ሊያሳምኑ ይሞክራሉ ። ሌላም አለ ብዙ ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል ። በቅርቡ አንዱ ቅሌታም የቤዛ ፊልም ተዋናይ ሚካኤል ታምሬ ወደ ራህናይል ሆቴል ይመጣና ባለቤቱ የታለ ብሎ ይጠይቃል ።ጥበቃውም ያሳየዋል ፣አቶ አበበ ይመኑን አርቲስቱ ሚካኤል “አወቅከኝ አርቲስት ነኝ ይለዋል” “አላወቅኩህም እንኳን አንተ የኔ ነው የተበለውን ይሄን አላወቀውም” በማለት ተናግሮ በአርቲስት ስም ሊበላ አፋን ከፍቶ ቀርቷል ።
ራህናይል ሆቴል ሲሰራ ከስፍራው የነበሩት የቀበሌ ቤቶች ሲፈርሱ ምትክ ያልተሰጣቸው ስለነበሩ የተወሰነ በቂ ያልሆነ ካሳ ቢከፈልም እስካሁን በቤት ክራይ እየተሰቃዩ እንደሆነ ይታወቃል ። ሌላው በአጠገቡ የሚያልፍ በስተቀኝ በኩል ያለ መንገድ ስላለ ከዚያ አካባቢ የሚገኙ ኮንቲነሮችን(የወንዶች የውበት ሳሎኖችና ንዋየ ቅድሳት መሸጫ ናቸው ) እንዲነሱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ። እሱም ለበሽታ ይዋኛል ህዝቡንም ለበሽታ እየዳረገ ይገኛል ሆቴሉ ፤ ከሆቴሉ የሚለቀቀው ፍሳሽ በሚገርም ሁኔታ በመንገዱ ዳር ካለው ኮሪደር ቱቦ ይቀላቀላል ። በአብዛኛው ለበሽታ የሚያጋልጥ ሽታ አለው ። ከዝምቡ ወያኔ ማር ባንጠብቅም እውነታው ይወጣ የሚያውቀው ያውቀዋል በሚል ነው ለመፃፍ የተገደድኩት ።
የህዝብ ንብረት በእውነት ጤና አይሆንም ።
የነፃነት ትግል ጉዞው የወያኔን እኩይ ሴራ በማጋለጥ ወያኔን እራቁቱን በማስቀረት ይቀጥላል ።
ሞት እና ውርደት ለወየኔ ህወሀት !
#እንቅዩጳዝዩን_ባህርዳር (፳፯/፰/፳፻፰ ዓ.ም)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *