ዐማራ እንዴት ዋለ? (ነሃሴ 6 ቀን 2008 ዓ.ም.) በከተማው የሚኖረውን የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ በመፍራት የደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ መኪናዎቹን ወደ ፖሊስ ኮሌጅ አሸሸ

ዐማራ እንዴት ዋለ? (ነሃሴ 6 ቀን 2008 ዓ.ም.)
በከተማው የሚኖረውን የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ በመፍራት የደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ መኪናዎቹን ወደ ፖሊስ ኮሌጅ አሸሸ
• በሳውዲና በኬንያ በስደት የሚገኙ ዐማሮች ላይ ወያኔዎች ጫና ለማድረስ እየሞከሩ ነው
• የሸበል በረታ ገበሬዎች ለማንነታቸው ተጋድሎ ቁርጠኛ ሆነው ተነስተዋል
• በየቦታው የሚታሰሩ ዐማሮች ቁጥር ሲጨምር የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊትም ትግሬዎችን በመጠበቅ ላይ ተሰማርቷል
• መሠረት የሌላቸው ወሬዎች የዐማራውን ተጋድሎ በአሉታዊ መልኩ እየጎዱት ነው
ደብረ ማርቆስ፤ የደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ ነገ ነሃሴ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ይኖራል የተባለውን የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ ምክንያት ተሸክርካሪዎቹን ለመታደግ ከከተማው ወደ አዲስ አበባ መውጫ በኩል ካለው የዐማራ ፖሊስ ኮሌጅ ግቢ ማሸሹን ዛሬ ከመሸ ከደብረ ማርቆስ ከተማ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ዩንበርሲቲው በተጨማሪም ተማሪዎቹን ከግቢ መውጣት እንደማይችሉ አስጠን ቅቋል፡፡ ከግቢ የወጣ ተማሪም ተመልሶ መግባት እንደማይችል መግለጹን የክረምት ትምህርት እየተከታተሉ ያሉ ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡
የደብረ ማርቆስ ዐማሮች በበኩላቸው ከፍተኛ የሆነ የአገዛዙ መከላከያ ሠራዊት ቢኖርም የተጋድሎው ሰልፍ እንደማይቀር በቁርጠኛነት አሳውቀዋል፡፡ ነገር ግን ማንም በሕዝብና በግለሰብ ንብረት ላይ ምንም ዓይነት አደጋ እንዳይደርስ ጥንቃቄ እንደሚደረግም አሳውቀዋል፡፡ ያልታሰበ ጥፋትና አደጋ ቢፈጠር ሆን ተብሎ ዐማሮችን ለመጨረስ የተለመደ ያበቃለት ታክቲክ እንደሚሆን ይህንንም ሕዝቡ እንዲረዳላቸው ያነጋገርናቸው ግለሰቦች ገልጸዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የደብረ ማርቆስ ከተማን የተጋድሎ ሰልፍ የተለያዩ ግለሰቦች በተለያየ ቀን መርሀ ግብር ማስተላለፋቸው ውዥንብር ውስጥ ጨምሯቸው እንደነበር ገልጸዋል፡፡
ነገ በብቸና ከተማም የተጋድሎ ሰልፍ ሊኖር ይችላል፡፡
ሸበል በረንታ (የእድ ውሃ)፤ የሸበል በረንታ አርሶ አደሮች መንግሥት በማንነታቸው ምክንያት የሚያደርስባቸውን ጫና ካላቆመ እንደማይደራደሩ የበላይ ዘለቀን ፈለክ ተከትለዋል፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት የወረዳ አስተዳዳሪ የነበረው እና አሁን በምስራቅ ጎጃም ዞን በኃላፊነት የሚገኘው የወያኔ ተቀጣሪ በሆነው አቶ ሰፊነው ብርሃኔ በተደረገው የሕዝብ ስብሰባ ‹‹እናንተ ስለወልቃይት ምን አገባችሁ?›› የሚል መልክት ቢያስተላልፍም ‹‹እስካሁን እናንተ ገረድ የሆናችሁት ይበቃል›› በማለት የሸበል በረንታ ዐማሮች ስብሰባውን አቋርጠው ሒደዋል፡፡ የበላይ ዘለቀ ልጆች የኩሬ የኩበትና ሌዲ ቡይቴ በሚባሉ አካባቢዎች ከደራ ዐማሮች ጋር መክረዋል፡፡ የአካባቢው ሕዝብ በሚገባ እንደተቀላቀላቸው ለማወቅ ችለናል፡፡
ዓባይ በርሃው ውስጥ ተፈጸመ ስለተባለው ነገር ደጀን ከተማ የሚኖሩ ዐማሮችን ስንጠይቅ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡
ፍኖተ ሰላም/ ኮምቦልቻ፤ በፍኖተ ሰላምና በኮምቦልቻ የሚታሰሩ ዐማሮች ቁጥር ጨምሯል፡፡ ዛሬ ከሁለቱም ከተሞች የታሰሩ ሰዎች ከ15 በላይ መደርሱን ለማወቅ ችለናል፡፡ ሆኖም የዐማራ ወጣቶች የበለጠ መነሳታቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡
አጠቃላይ፤ የዐማራው ተጋድሎ በየቦታው ተቀጣጥሏል፡፡ ሆኖም ብዙ ግለሰቦች ምንም መረጃ ሳይኖራቸው የሚያሰራጯቸው መረጃዎች ተጋድሎውን በአሉታዊ መልኩ እንደሚጎዳው እየገለጹ ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፍን በተመለከተ፣ አንዳንድ አካባቢዎች የሚደረጉ ኩነቶችን በማብዛት ወይም በማሳነስ የሚወሩ ወይም ያልሆነውን ከመዘገብ የዐማራው ተጋደሎ የሚያከናውነው ውጤት በቂ መሆኑን እርሱንም መዘገብ አስፈላጊ እንደሆነ ከተለያየ የዐማራ አካባቢዎች የሰበሰብናቸው መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
ከውጭ ወደ አገኘናቸው መረጃዎች ስናልፍ
በሳውዲ አረቢያና በኬንያ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የትግራይ ደኅንነቶች ወከባ ለመፍጠር እየሞከሩ እንደሆነ እየተገለጸ ነው፡፡ ከሪያድ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በርካታ ዐማሮች የሚገኙባቸውን እንደ ሪያድና ጂዳ ባሉ ከተሞች በአቶ ጻድቃን፣ አቶ ሰመረ እና ዶክተር መሀመድ በሚባሉ የትግሬ ደኅንነቶች የሚመራው ልዑክ ዐማሮችን እያሳደደና እያሸማቀቀ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡ በቤት ሰራተኝነት ያሉ ሴቶችን ሁሉ እየደወሉ ዘመዶቻቸውንና ወንድሞቻቸውን አርፈው እንዲቀመጡ እንዲነግሩ ያ ካልሆነ ግን የሥራ ፈቃዳቸውን እስከ ማስቀማት እንደሚደርሱ እየዛቱባቸው ነው፡፡ በማኅበራዊ ሚዲያ የአክቲቪዝም ሥራ ከሚሠሩ የዐማራ ተወላጆች ላይ የበለጠ እንደሚበረታ ነው የሰማነው፡፡ የትግራይ ተወላጆችን በማደረጀት በከፍተኛ የዐማራ ጥላቻ እራሳቸውን እንዲታደረጉም እንደተነገራቸው ለማወቅ ችለናል፡፡
በኬንያ የሚኖሩ ዐማሮችም ተመሳሳይ ችግር ላይ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡ ዛሬ በስደት በኬንያ የሚገኘውን አክቲቪስት ጥላየ ታረቀኝ ላይ የመግደል ሙከራ ተደርጎበታል፡፡ ጥላየ እንደሚናገረው ሁለት ወንዶችና አንዲት ሴት ሆነው እቃ ሊገዛ ከገባበት ሱፐር ማርኬት ሲወጣ ያዙት፡፡ ከዚያም በሰንሰለት አስረው ኩስማዩ ወደሚባለው የኬንያ አካባቢ እንውሰድህ ሲሉት በአልሞት ባይ ተጋዳይነት የያዙትን ሰንሰለት ነጥቆ ጣለው፡፡ ከዚያም በሽጉጥ ሲያስፈራሩት የኬንያ ፖሊሶች ደርሰው እንደታደጉት ጥላየ ገልጧል፡፡ ጥላየ እንደሚለው ሊይዙት የነበሩት ደኅነነቶች ታርጋ የሌለው መኪና ነበራቸው፡፡
የዐማራ ትግል ከእንግዲህ ወደፊት ነው//
የዐማራ ሕዝብ ትግል ያሸንፋል//
(ቀጥሎ ያለው ፎቶ አቶ ጻድቃን የሚባለው የትግሬ ደኅንነትና በጂዳ ዐማሮችን የሚያሰቃየው ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *