“ብአዴን ስልጣኔን ሊቀማኝ ነው” ሕወሃት ብአዴን ለሕወሃት ራስ ምታት ሆኖበታል። “የብአዴን መሪዎች የሕወሃትን የበላይነት ለመንጠቅ አማራን አሳምጸውብኛል።

“ብአዴን ስልጣኔን ሊቀማኝ ነው” ሕወሃት…ከቅዱስ መሀሉ
ብአዴን ለሕወሃት ራስ ምታት ሆኖበታል። “የብአዴን መሪዎች የሕወሃትን የበላይነት ለመንጠቅ አማራን አሳምጸውብኛል።” ያለው ሕወሃት የአማራ ክልልን ፕሬዝዳንት እና ባለስልጣናት “የሜዳ አህያ ባህሪ ያላቸው የበሰበሱ ነፍጠኞች ናቸው።” በማለት ወርፏቸዋል። በመቀሌ መሽጎ ከኦሮሞ ሕዝብ እና ከአማራ ሕዝብ የተነሳበትን ተቃውሞ ማምለጥ እንደማይቻል የተረዳው ሕወሃት ጨንቆት የብሄራዊ ባንክ የወርቅ ክምችትን ሳይቀር ወደመቀሌ እያጋዘ መሆኑ ተሰምቷል። በአማራ ክልል በተለያዩ ስፍራዎች ለተገደሉ እና ንብረታቸው ለተዘረፉ ትግሬዎች ይቅርታ እንዲጠይቅ የተጠየቀው ብአዴን “ይቅርታ አልጠይቅም!” በማለት ምላሽ መስጠቱ እና በአማራ ክልል አመጹ ሲስፋፋ በዝምታ መመልከቱ ሕወሃትን እንዳደገበት ቅምቡርስ ቀላልነቱ እና ትንሽነቱ ይበልጥ እንዲታየው አድርጎታል።ሕወሃት ሌላም ነገር አስጨንቆታል። “ብአዴን 35ኛ አመቱን ሲያከብር የትግሬዎችን ገድል በቴሌቪዥን በማሳየት የኔን ተጋድሎ የራሱ አስመስሎ ያቀረበው አሁን ሕወሃትን ለመጣል ለሚያደርገው ጥረት እንዲያመቸው አስቦ ነበር።” በማለት “የብአዴን መሪዎች የፍቅር ደብዳቤ እና ጥቂት ግጥሞች ከመጻፋቸው ውስጥ በትግሉ ወቅት ድርሻ አልነበራቸውም።” ሲል አላዝኗል። ሕወሃት ብአዴንን ሰደብኩ ብሎ ከትግሬ ውጭ ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እያንኳሰሰ እና ‘ጀግና እኛ ብቻ ነን” እያለ መሆኑ አልተገለጠለትም። በጭንቅ ውስጥ እንኳ ሆኖ ‘ብሄር ብሄረሰብ’ እያለ የሚያታልለውን ሕዝብ እንኳ መናቅ የማይተው የእኩዮች ቡድን መሆኑንም አሳይቶናል። “ብአዴን ከሕወሃት እና ከትግራይ ሕዝብ ለአማራ ሕዝብ የተሰጠ ስጦታ ነው።” ያለው ሕወሃት ለዚህ ውለታው የአማራ ሕዝብ እንዲያመሰግነው ሳይፈልግ አልቀረም። ከአሜሪካ ወይም ከእንግሊዝ በእርዳታ የሚሰጡ የስንዴ/የበቆሎ ማዳበሪያዎች እና ኬሻዎች ላይ ‘ዩኤስ ኤድ ፍሮም ዘ አሜሪካን ፒፕል’ የሚል ጽሁፍ ትዝ አላችሁ። ብአዴን መሪ የሌለውን የአማራ ሕዝብ መሪ እንዲሰይም ፍሮም ዘ ትግራይ ፒፕል የተሰጠ የአማራ ስጦታ ነው። እናት ለልጇ ምጥ አስተማረች ነው ነገሩ። ብአዴን እና ሕወሃት ሳይፈጠሩ የአማራ ሕዝብ መሪ አልነበረውም? የአማራ ህዝብ ስርዓት የተማረው ሃይማኖታዊ እሴቶች፣ሞራላዊ ሰንሰለቶች እና ማህበረሰባዊ ግብረገብነትን ፈጽሞ ከማያውቀው አግድም አደጉ ሕወሃት ነውን? ይህ ግብረ ገብነት ቢኖረው ኖሮ ዛሬ ብአዴን ጆሮ አልሰጥም ሲለው ‘ካላመናችሁ ወሎ፣ሰሜን ሸዋ እና ጎንደር ሂዳችሁ ተመልከቱና እውነቱ ይገለጥላችኋል።” ባላለ ነበር።

ሕወሃት እንዲህ ጭንቅ ከሚለው እና በብአዴን አስታኮ የአማራን ሕዝብ የበሰበሰ፣ርፍራፊ፣አህያ ወዘተ እያለ ከሚሳደብ ብአዴኖችን “እኔ እንደፈጠርኳችሁ የማታምኑ ከሆነ እና የበላይነቴን የማታከብሩ ከሆነ ትግራይን እገነጥላለሁ” ብሎ ለምን አያስፈራራቸውም? እኛም እንቆቅልሽ ሆኖ እስካሁን እርግጠኛ የሆነ መልስ ያጣንለትን የትግራይን ሕዝብ ምላሽ እንስማ! ለማንኛውም ሕወሃት የበሰበሰ የሚለው አማራ እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም ነፍጠኛ ነው። “አማራን ሽንቱን አሸንተነዋል” እያልችሁ ከበሮ ስደልቁ ኖራችሁ ዛሬ ምነው ድንገት ሰላማዊ የሆነው የአማራ ህዝብ ወዘተ ማለት አበዛችሁ። ሰላማዊ የሆነውን የአማራ ህዝብ አይደለም እንዴ ባህር ዳር ላይ የጨፈጨፋችሁት? ለስራ ብላችሁ በባህርዳር ተከራይታችሁ ከምትኖሩበት ሕንጻ ላይ የባህር ዳርን ወጣት በጥይት የደበደባችሁት አሸንተነዋል ያላችሁት አማራ ወገኖች ስለሆኑ አይደለምን? ይሄ የምታፈሱት ደም ፈሶ የሚቀር ይመስላችኋል? በርግጥ የአማራ ህዝብ አሁን የሚገድለውን ጠላቱን በደንብ አውቋል።

ብአዴን እና አባላቱ ያላቸው ምርጫ ግን ሕዝቡ ካለው ምርጫ እጅግ የጠበበ ነው። ብአዴን በግልጽ ሕዝቡን ለመጨፍጨፍ ከትግራይ የሚመጡ ወታደሮችን በይፋ ከክልሉ እንዲወጡ ማድረግ ወይም ሕዝቡ ራሱን በማንኛውም መንገድ እንዲከላከል በይፋ ማሳወቅ ይህም ካልሆነ ሕወሃት አሁን ደንብሮ የሚይዘውን እንዳሳጣው በዝምታው መዝለቅ ይጠበቅበታል። ሌላኛው ምርጫ ልክ በኦህዴድ ላይ እንደተደረገው ለብአዴን ውርደትን የሚያተርፍ ነው። አባላቶቹን እና አመራሮቹን ሕወሃት የበቀላቸዋል። ከሕወሃት ጋር ከወገኑ በኋላ ብአዴኖች ላይ ለሚደርሰው ውርደት የሕዝቡ ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል ለናንተው ልተወው። የአማራ ሕዝብ ግን ለጠላትህ እጅግ በጣም መምረር እና እሬት መሆን ይጠበቅብሃል። እጅግ በጣም በጭካኔ የተካነ ዘረኛ ጠላት ሲገድልህ እንደ ሰው እንካ እንደማይቆጥርህ ማወቅ አለብህ። ዘረኛ ያልሆነ እና በጥላቻ ያልመከነ ‘ሰው’ ወደማያውቀው ቦታ ሄዶ የማያውቃቸው ሰዎች ላይ የጠብመንጃ ላንቃ አይከፍትም።በባህር ዳር የሆነው ይህ ነው። ግድያው እና ጭፍጨፋው በአማራነት ላይ መሆኑን የተረዱ የአማራ ልዩ ሃይል እና ፖሊሶች ‘ወገናችንን አንገድልም’ ሲሉ በምታዩት አንቶኖቭ ከመቀሌ ተጭነው መጥተው ነው ወጣቱን የጨፈጨፉት! ስለዚህ ዘረኛነት እና በዘር ላይ የተቃጣ ጥቃት መኖሩ ግልጽ ነው። ይሄ ደግሞ ወዴት ሊያመራ እንደሚችል መተንበይ አያስፈልግም። በርካታ የአማራ ወታደሮች እና የሟች ዘመዶች ደም ለመመለስ አግአዚያኑን በአብራጅራ ገጥመዋቸዋል። በውጊያው የብዙዎች ሕይወት እየተቀጠፈ፤ ደምም እየፈሰሰ ነው። ሲ ፓሴም ፓራ ቤሉም – ሰላምን የሚፈልግ ለጦርነት ይዘጋጅ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *