ሰላም የሚፈልግ ለጦርነት ይዘጋጅ!! የደቡብ ወሎ እና የደብረ ማርቆስ ፖሊሶች ሕዝብ ላይ አንተኩስም ብለዋል!

ሰላም የሚፈልግ ለጦርነት ይዘጋጅ!!….. ከቅዱስ መሀሉ
የደቡብ ወሎ እና የደብረ ማርቆስ ፖሊሶች ሕዝብ ላይ አንተኩስም ብለዋል!
በአባይ በርሃ የአግአዚያኑ አስከሬን ተለቅሞ አላለቀም!

በደቡብ ወሎ ፖሊሶች ሰልፈኛውን አንገድልም በማለታቸው ጠመንጃቸውን እንዲያስረክቡ ተጠይቀዋል።ስለዚህ እንደ ባህር ዳሩ ሁሉ ከትግራይ የመጡ የአግአዚ ወታደሮች ሰልፈኛውን የሚጨፈጭፉ ከሆነ በፍቅር እና በአክብሮት ከትግሬዎች ጋር አብሮ የሚኖረውን የወሎ ሕዝብ በግልጽ ደም ያቃቡታል። በዘረኞች በግልጽ አንድ ጎሳ በሌላ ጎሳ ላይ የሚያደርገው ግድያ የኖረን የማህበራዊ ትስስር እና የጋራ ዕሴቶች በማፈራረስ የልዩነት አጥር የመገንባት አቅም አላቸውና ልብ ያለው ልብ ይበል!!! ከደቡብ ወሎ ፖሊሲች ላይ መሳሪያ የሚነጥቁት ‘አንገድልም’ በማለታቸው ብቻ ሳይሆን ሕዝቡን በአማራነቱ ሲገድሉት በባህር ዳር አንድ ፌደራል ፖሊስ እንዳደረገው እነሱም ገዳዮቹን እንዳይገድሉ ፈርተው ነው።በባህር ዳር ከትግራይ መጥተው የማያውቁትን ሕዝብ ያለርህራሄ ሲጨፈጭፉ የተመለከተ አንድ ፌደራል ፖሊስ አምስት አግአዚዎችን ገድሎ ራሱን ማጥፋቱ ይታወቃል።የአብደራፊ ከተማ ሕዝብም በከተማው የሚገኘውን የአግአዚ ወታደሮች አባሯል። የአማራ ክልል ታርጋ ያልቸው መኪኖች ወደ ሁመራ እንዳይገቡ ተከልክለዋል። በወልድያ የተጠራውን ሰልፍ ለማስቆም የአካባቢው ባለስልጣናት የጠሩት ስብሰባ ላይ የተገኘው ሕዝብ “በጎንደር የተሰለፈውን ሕዝብ ጥቂት ነው አላችሁ አይደል? በባህር ዳር የወጣውን ህዝብ ጥቂቶች ብላችሁ ተሳለቃችሁ አኡደል? የእኛን ምን እንደምትሉት እናያለን!” ብሎ ባለስልጣናቱ ምንም ሳይተነፍሱ አዳራሹን ለቆ ወጥቷል። ባለስልጣናቱም እንደ ተራ ዱርየ “ትሰልፉና እንተያያለን” እያሉ በአዳራሹ አቅራቢያ ላገኛቸው 20የማይሞሉ ሰዎች ሲያስፈራሩ ተስተውሏል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የደብረ ማርቆስ ፖሊስ እና በአካባቢው የሚገኝ ልዩ ሃይል ከአዲስ አበባ ለሄዱ ባለስልጣናት “ሕዝቡ ከተሰለፈ ከሕዝቡ ጎን እንቆማለን! ወንድሞቻችንን አንገድልም!” በማለቱ ስብሰባው ተብትኗል። በአሁኑ ሰዓት ከከተማው ሕዝብ ጋር የሚስተካከል ወታደር ደብረ ማርቆስን ወሯታል። በሽዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ወጣቶች ቢታፈሱም ወላጆች እና ሴቶች ሳይቀሩ ሰልፉን ማንም ምድራዊ ሃይል አይከለክለንም ብለዋል።

እያንዳንዱ የሚፈስ ደም ሌላ ደም ይጠራል። ዛሬ ሌሊቱን በአባይ በርሃ ጫፍ ላይ ጎሃጺዮን ላይ ያደፈጡ የጎጃም ልጆች በኦራል ተጭነው ሲሄዱ የነበሩ ከ30በላይ የአግአዚ ወታደሮችን ገድለው ወደ በርሃው በመውረድ ላይ ሳሉ ከፍቼ የተነሳ ሌላ የአግአዚ ወታደር የአካባቢውን ሕዝብ ማን ነው ያደረገው እያሉ በማስጨነቅ ላይ ሳሉ “ወንድ ከሆንክ ና ግጠመን” የሚል የተኩስ ምልክት ሰጧቸው። በዘረኝነት አይምሮው የተደፈነ የማያውቀው ቦታ ሄዶ ለመግደል ማሰብ ስለማይችል በጥላቻ የጨነገፈው እና አማራን መግደል ጽድቅ ነው እየተባሉ ያደጉት አግአዚዎች በጨለማ አባይ በርሃ ገቡ። በአባይ ዙሪያ እየቦረቀ ያደጉት የጎጃም አናብስቶች ከ47በላይ አግአዚዎችን አንድም ሳይተርፉ ጨፍጭፈዋቸዋል። በአሁኑ ሰዓት የጎጃም መንገድ ተዘግቶ ወያኔ ሬሳ እየለቀመ ነው። ሕወሃት ሆይ! ትዕቢት እና ዕብሪት ያዋርዳሉ። ይህ የሚፈሰው ደም ገና የብዙዎችን ሕይወት ይነካል፤ያናጋልም!! የትግራይን ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያ ጋር አብሮ ይኖር ዘንድ ደም ባታቃቡት እና ባታፋጁት መልካም ነው። ከዚያ ውጭ የትግራይን ህዝብ ከሌላው ጋር በማናከስ ስልጣኔን አስቀጥላለሁ ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። በኢትዮጵያ ላይ የትግራይ ሕዝብ ብቻውን ወሳኝ መሆን አይችልም። ኢትዮጵያ የጋራችን ናት። ሕወሃት አንድ ነገር አምኖ መቀበል አለበት።አለዚያ ሰላም ሳይሆን ለለየለት ጦርነት ዝግጅት ጥቂት ክፍተት ብቻ ሊኖር ይችላል። የሃገሪቱ ብዙሃን ሕዝብ ባርነት አንገሽግሾቸዋል። ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ እስከኖርን እና የኢትዮጵያን ዜግነት እስከተጋራን ድረስ ወደደም ጠላም ሕወሃት ትግሬ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር እኩል መሆኑን መቀበል አለበት። አለዚያ ሰላም በምኞት እና በከበሮ ድልቂያ አይመጣም። ሰላም የሚመጣው ነጻነት እና እኩልነት ሲኖር ነው። የጳጳስ እና የቃልቻውን ዓይነት ሰላም አንፈልግም። እነዚህ ሰዎች ሕወሃት የአማራ እና የኦሮሞ ሕዝብ ላይ ላወጀው ጦርነት ቡራኬ ሰጡት።”እሰይ! ደግ አደረክ! እንደፈለክ ግደልና ስልጣንህን አስጠብቅ። የበላይነታችንን አስቀጥል!” አሉት። መልክታቸው ይሄው ነው። የነሱ ንግግር ድሮ የአውሮፓ ሃገራት ለጦርነት ሲሰማሩ የካቶሊክ ቄሶች እንደሚባርኩት ዓይነት የጦርነት ቡራኬ ነው። ለማንኛውም በባርነት ውስጥ ከሚገኝ ሰላም ለነጻነት የሚደረግ ጦርነት ዋጋ አለውና ምርጫችን እሱ ነው። ሲ ፓሴም ፓራ ቤሉም!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *