ዝርዝር የውሎ ዘገባ፡- ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረታቦር) በባሕር ዳር ለነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ተጋድሎ ሰልፍ ዝግጅት ተጠናቋል

(ዝርዝር የውሎ ዘገባ፡- ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረታቦር)
በባሕር ዳር ለነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ተጋድሎ ሰልፍ ዝግጅት ተጠናቋል
• ጎንደር የሚኖሩ ትግሬዎች በአየር መንገድ እንዲወጡ እየተደረገ ነው
• የደብረ ታቦር፣ ጋይንትና አካባቢው ያለው የዐማራ ተጋድሎ አሁንም አልበረደም
ባሕር ዳር፡ እሁድ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. በጎጃም እምብርት የሚደረገው የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ ሊጀመር ሰአታት ብቻ ቀርተውታል፡፡ ከቦታው በስልክ ባደረግነው የመረጃ ልውውጥ ሁሉም የባሕር ዳር ከተማና አካባቢው የሚኖሩ ዐማሮች በጠዋት መስቀል አደባባይ ለተጋድሎ ይገናኛሉ፡፡ ባነሮችና ቲሸርቶች ታትመው አልቀዋል፤ የአባቶቻችን ሰንደቅ ዓላማም ተዘጋጅቷል፡፡ በመታተም ላይ የነበረ በርካታ መጠን ያለው ቲ ሸርት በባንዳ ደኅንነቶች ጥቆማ የታሸገ ቢሆንም በቂ መጠን ያለው ታትሞ ወጥቷል፡፡ የባሕር ዳር ሕዝብ በገንዘብና በሞራል ያደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሰልፉን እየመሩ የሚገኙት ዐማሮች በራሳቸው ተነሳሽነት ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሲሆን ከዐማራነት ውጭ የሚነሱ ጥያቄዎችን የሚያስቆሙ ብሎም በእነሱም ላይ እርምጃ የሚወስዱ ኮሚቴዎች ተዋቅረዋል፡፡
ጎንደር፡ የጎንደርና አካባቢው ችግር እየተወሳሰበና በቀላሉም ሊፈታ የማየችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ዛሬ ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. አንድ የትግራይ ተወላጅ የሆነ ወያኔ ለተጋድሎ በወጡ ዐማሮች ላይ ቦንብ በመወርወር ከሦስት በላይ ሰዎችን ገደለ፡፡ የወያኔ መከላከያ ሠራዊት ይህን ነፍሰ በላ ሰው ተከላክለው ለማዳን ቢሞክሩም አልቻሉም፤ ከነቤቱ መቃጠሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ በአዘዞ ትናንት የተሰው ሰማእታትን ለመቅበር በሚሔዱ ሰዎች ላይ የተኩስ እሩምታ የከፈተው መከላከያ ሠራዊት ሞትን የማይፈሩት የዐማራ ወጣቶች አዘዞ የሚገኘውን የመከላከያ ሠራዊት ካምፕ መቆጣጠራቸው ተሰምቷል፡፡ የሥርዓቱ አገልጋይ የሆኑ ግለሰቦች የሆኑ የንገድ ተቋማት በብዛት መውደማቸው የታወቀ ሲሆን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የተኩስ ልውውጥ መኖሩን ለማወቅ ችለናል፡፡
ይህን ተከትሎ የሥርዓቱ አገልጋይ የሆኑ የትግራይ ተወላጆችን መንግሥታቸው በአየር መንገድ በኩል ሲያጓጉዝ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዛሬ ከጎንደር አጼ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ ወደ መቀሌና አዲስ አበባ በርካታ የትግራይ ተወላጆች መውጣታቸውን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡
ቆላድባ፡ በደንቢያ ወረዳ የቆላ ድባ ዐማሮች ተጋድሎ ከሁሉም ያየለ እንደነበርም ሰምተናል፡፡ በሌሊት በቁጣ የወጣው የደንቢያ ዐማራ ማንም የሚያቆመው ኃይል ሳይኖር የሥርዓቱ መገልገያ የነበሩ ተቋማትንና ተሸከርካሪዎችን ዶጋ አመድ አድርጓል፡፡ እስካሁን ባለመን መረጃ መሠረት ከዐሥር ያላነሱ መኪናዎች ተቃጥለዋል፤ የብአዴን፣ የአብቁተና ሌሎችም መሥሪያ ቤቶች ወድመዋል፡፡ ከወያኔ መከላከያ ሠራዊት ጋር በበነበረ ተጋድሎ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዐማሮች የቆሰሉ ሲሆን የሞቱ ሰዎች መኖር አለመኖራቸው የደረሰን መረጃ የለም፡፡ በተመሣሣይ ከጭልጋ ሰራባ ካምፕ ወደ ጎንደር በመጓዝ ላይ ከነበረ የትግሬ መከላከያ ጋር በተደረገ ተጋድሎ አይባ ላይ ሁለት ያክል ዐማሮች ተሰውተዋል፡፡
አርማጭሆ፡ በላይ፣ ታችና ምእራብ አርማጭሆ፣ በጠገዴና በጠረፍ አካባቢዎች ዐማሮች አካባቢያቸውን ነጻ ማውጣታቸውን የተሰማ ቢሆንም የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ የሱዳን መንግሥት በምዕራብ አርማጭሆ በኩል ከዐማሮች ላይ ጦርነት መጀመሩን የተሠማ ቢሆንም እስካሁን በስልክ ችግር ማረጋገጥ አልተቻለም (ዜናውን የጠናቀረው ሰው ማረጋገጥ አልቻለም)፡፡
ደብረ ታቦር፡ በደብረታቦር የተካሔደው የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ በከተማዋ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነበር፡፡ ለተጋድሎ የወጣው ሰው ብዛት እስከ 5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን እርዝመት ነበረው ተብሏል፡፡ ቀሳውስት፣ አዛውንቶች፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች ተሳትፈውበታል፡፡ የአጼ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ ‹‹ዘመዶቻችን አገር መሸጥ አላስለመዱንም!›› እያሉ ወጣቶች የአባቶቻቸውን ሰንደቅ ዓላማ ያውለበለቡ ሲሆን ሰንደቅ ዓላማዋን ለመቀየር ከመጣ የአጋዚ ጦር ጋር በነበረ ተጋድሎ ከአራት ያላነሱ ሰዎች ተሰውተዋል፡፡ የተሰው ዐማሮች አስከሬን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለብሶ በክብር መሸኘቱን ለማወቅ ችለናል፡፡ ከክምር ድንጋይና ጋሳይ አካባቢ ገበሬው ፈረሱን ሸልሞ የመጣ ቢሆንም የአጋዚ ጦር እንዳይገባ ለመከላከል ሞክሯል፡፡ አንድ የፌደራል ፖሊስ አልሞ ዐማሮችን ለመምታት ሲሞክር ሞት የማይፈሩት የፋርጣ ዐማሮች መሣሪያውን ነጥቀው እርሱንም መተው መሔዳቸውን አውቀናል፡፡ የክልሉ ፖሊሶች ከሕዝብ ጎን እንደነበሩም ታውቋል፡፡ ከቀኑ በስምንት ሰአት ሰልፉ ተጠናቋል፡፡
ጋይንት፡ የነፋስ መውጫ ከተማ ዛሬ ከዝናብ ጋር ተጋድሎዋን በጠዋት ነበር የጀመረችው፡፡ ነፋስ መውጫ ዐማሮች ትናንት የታሰሩ ዐማሮችን አስፈትተው ንብረትነቱ የወያኔ የሆነን የእንጨት ክምር አቃጥለዋል፡፡ የክልሉ ፖሊስ አብሮ ለተጋድሎ መሠለፉን ብንሰማም በኋላ ላይ ቁጥራቸው ያልታወቀ ለተጋድሎ የወጡ ወጣቶች መሰዋታቸው ተነግሯል፡፡ ዜናውን ያጠናቀረው ስንት ሰዎች መስዋት እንደሆኑ ሊያወቅ አልቻለም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *