የጎንደር ሕዝብ ሆይ! ኤርፖርቱን ያዝና ወያኔን አስጨንቀው

የጎንደር ሕዝብ ሆይ! ኤርፖርቱን ያዝና ወያኔን አስጨንቀው!
የአማራ ህዝብ ጠላትነት በጽሁፍ እና በመግለጫ ሲነገር ቢኖርም አሁን ከወደ አዘዞ በሚሰማው ዜና ሕዝቡ ላይ በግልጽ ጦርነት ታውጆበታል። የ24ኛው ክፍለ ጦር አዘዞን በከባድ መሳሪያ እየደበደበ ሲሆንየአዘዞ ሕዝብም ሴት ወንድ ሳይል ምሽቱን ሃይለኛ ውጊያ እያደረገ ነው። ተጨማሪ የወያኔ ወታደሮች ወደ ጎንደር እያቀኑ ሲሆን የአካባቢው ገበሬዎችም ወደዚያው እየተጠጉ ነው። በባህር ዳር ካሳ ተክለ ብርሃን የተባለ የፌዴራል ጉዳዮች ሚንስትር መኖሪያ ቤት በከተማው ወጣት በድንጋይ እየተወገረ ነው። የጎንደር ሕዝብ የቀበሌ 18 ጽ/ቤትን በእሳት አውድሞታል።

የጎንደርን ሕዝብ ጥሪ የሰማው የሳንጃ ሕዝብም ከተማዋን ሙሉ ለሙሉ ከወያኔ መዳፍ ነጻ አድርጓል። ሕዝብ ሲያስገድሉ የነበሩ ሰዎች እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሆነ እና የተወሰደባቸውም በማህበራዊ ድረገጾች ስማቸው ይፋ ተደርጓል። በጎንደር ሌሊቱን የሚፈጠረው አይታወቅም። ለሊቱን ምን እንደሚፈጠርም አይታወቅም። ሆኖም ግን ለጎንደር ሕዝብ የአጼ ቴዎድሮስን አየር ማረፊያ ለመደራደሪያነት በቁጥጥሩ ስር ያድርግ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አበዳሪዎች ሳይወዱ በግዳቸው የመንግስትን ወንበዴነት እንዲያውቁ ማድረግ ይቻላል። በርግጠኝነት ለወያኔ ከዚህም በላይ ብዙ መዘዝ ያመጣበታል። ይህን ለማድረግ የግድ በአውሮፕላን ማረፊያው ላይ አውሮፕላኖች እስኪያርፉ መጠበቅ ያስፈልጋል። ሕዝቡ የአውሮፕላን መንደርደሪያዎችን ይስፈርባቸው። ይህ በዚያ የሚገኙ እና ከዚያ የሚወጡ በረራዎችም እንዲሰረዙ ያስገድደዋል። በዚህም በአውሮፕላን ተጭነው ከመቀሌ እና ከባህር ዳር የልጆችህን ደም ሊያፈሱ የሚመጡ ተጨማሪ ነፍሰ ገዳይ ወታደሮችን ማስቆም ይቻላል። ወታደሮች ከአካባቢው ካልወጡ ሕዝቡ ከአውሮፕላን ማረፊያው እንዳይወጣ!!! እንደለመደው እንተኩሳለን ካለ ኪሳራው ምን እንደሁ ያውቀዋል። ይሄን ጥሪ ፈርቶ ወደ ጎንደር የሚደረግ በረራ ካቆመም በዚያ ምክንያት የሚገኘው ድል ከጎንደር ሕዝብም ድል በላይ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *