አማራው ዘሩ በሕወሓት ከመጥፋቱ በፊት በአንድነት ይነሳ” ሲል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ጥሪ አቀረበ

አማራው ዘሩ በሕወሓት ከመጥፋቱ በፊት በአንድነት ይነሳ” ሲል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ጥሪ አቀረበ

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

ወያኔ ህወሃት ዘርን መሰረት አድርጎ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈጽመውን የጥቃት ፖሊሲ ለመመከት በአንድነት እንነሳ!

የአማራ ህዝብ በቅድመ ዘመነ መሳፍንት ኢትዮጵያ አንደ ሆና እንድትቀጥል ከፍተኛ መስዓውትነት ሲከፍል የቆየ ህዝብ ነው፡፡ ዘመነ መሳፍንት እንዲከስምና ሰሜናዊና ደቡባዊ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ከፍተኛ መስዋትነት በመክፈል ለሀገሩ ያለውን ፍቅር አሳይቷል፡፡
አማራ በሀገሪቱ የመንግስት ስርዓት ለውጦች እንዲመጡ በኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ስሜት መስዓውትነትን የከፈለ አርቆ አሳቢ ህዝብ ቢሆንም ጨፍጫፊው ዘረኛ ቡድን ህወሃት ወያኔ ገና ከውልደቱ ጀምሮ የአማራን ህዝብ በመሰረታዊ ጠላትነት ፈርጆ በኢትዮጵያ ውስጥ ይህን ህዝብ እንዴት ማዳከም እንደሚችልና ከቻለም አጠቃላይ ህዝቡንና ሀገሪቱን በህወሃት ዘላለማዊ አገዛዝ ስር ማስገባት ነው፡፡ ይህን ካልቻለ ደግሞ የታላቋ ትግራይን ሪፐብሊክ እውን ማድረግ የሚል የፖለቲካ ፕሮግራም መሰነቁና ለዚህም ያለ ድካም መልፋቱ ነው፡፡
ሆኖም ይህን አጉል ምኞቱን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያደርገው ግስጋሴ በዋነኛነት እንቅፋትና የስጋት ምንጭ አድርጎ የፈረጀው ኢትዮጵያዊነቱን ኩራቱና የማንነቱ መገለጫ አድርጎ የሚያምነውን የአማራ ህዝብ በመሆኑ ብዙ ጥቃቶችን ሲፈጽም ቆይቷል።
በዚህም እንቅስቃሴው የኢትዮጵያዊ የብሄርተኝነት ጠንካራ ምሽግ ሲል በጠላትነት የፈረጀውን የአማራ ህዝብ በጅምላ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ማዳከምና ከምድረ ገጽ ለመደምሰስ በሰራ መጠመዱ ነው።
ይህም ህወሃት መሰረታዊ ጠላቴ ሲል የፈረጀውን አማራ ከወልቃይት ጽገዴ ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ እስከ አሁኗ ስዓት ድረስ በጎንደር እያካሄደ ያለው ጸረ አማራ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ዋናውና አንገብጋቢው መሆኑ በግልጽ ይታያል፡፡
ህወሃት የወልቃይት ፀገዴ በርካታ ንጹሃን ወገኖቻችንን በዘር አማራ ስለሆኑ ብቻ ጅምላ ከመረሸን አልፎ አፍኖ በመውሰድ አድራሻቸው እንዲጠፋ ብሎም ወደ አደገኛና ዘግናኝ እስር ቤቶች የወረወራቸው በመሆኑ ይህን አደገኛ ዘር ላይ ያነጣጠረ ናዚያዊና ፋሽስታዊ ጥቃት መላው የአማራ ህዝብ በጋራ ታጥቆ ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ጎን በመሰለፍ ሊመክተውና ሊደመስሰው ይገባል። ይህ በአማራነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በአማራነት ታጥቆ በመነሳትና በመደራጀት ብቻ የሚመከትና የሚመታ በመሆኑ ማነኛውም አማራ ዘሩ በህወሃት ሴራ ከምድረ ገጽ ከመጥፋቱ በፊት የህወሃትን ሴራና አሻጥር ለመደምሰስ በአንድነት እንዲነሳ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አ ዴ ሃ ን) የትጥቅ ትግል ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
አማራ ዘሩ በህወሃት ሳይጠፋ ለትጥቅ ትግሉ እንነሳ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *