የባሕር ዳር ሰልፍ ዝግጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል

AmharaResistance; Update:

1. የባሕር ዳር ሰልፍ ዝግጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል

ዐማሮች በጎጃም እምብርት ባሕር ዳር ነሐሴ 1 ቀን 2008 የሚያደርጉትን ሰላማዊ ሰልፍ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ባነሮች እየታተሙ ነው፤ የዐማራ ተጋድሎ ጎልቶ ይውላል፡፡

በሌላ በኩል የባሕር ዳር ከተማ በፌደራል ፖሊሶች ተከባ ሰንብታለች፡፡ የዐማራ ልዩ ኃይልና ሲቪል ፖሊሶች በወገናቸው ላይ ምንም ዓይነት እርምጃ እንደማይወሰዱ በተለያየ መልኩ እየገለጹ ነው፡፡ ጀግና የጎጃም ሕዝብም ለቀጣይ እሁድ ቆርጦ ተነስቷል፡፡ ምንም ዓይነት ኃይል የእሁዱን ሰልፍ የሚያስቀረው የለም፡፡

2. በደብረ ታቦር እና እስቴ የሚካሔዱ የዐማራ ተጋድሎ ሰልፎችን ለማወክ የሚሞክሩ ቅጥረኞችን በዘመዶቻቸው እንዲመከሩ ተጠይቋል

አቶ እዘዝ ዋሴ የተባለው የደ/ጎንደር አስተዳዳሪ ያለ ክልሉ እውቅና ወደ እስቴ የፌደራል ፖሊስ እንዲሔድ አድርጓል፡፡ ይህ ግለሰብ አቶ ቀለመ ወርቅ ምሕረቴ ከተባለው የምዕራብ እስቴ ወረዳ አስተዳዳሪ ጋር በመተባበር የዐማራ ወጣቶችን ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠት የሚያደርገውን እኩይ ተግባር በአስቸኳይ አቁሞ ከወገኖቹ ጎን እንዲሰለፍ በአካባቢው የሚኖረው የዐማራ ሕዝብ ጠይቋል፡፡

አቶ በላይነህ የሚባለው የደብረ ታቦር ከንቲቫ ደግሞ የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች ጉዳይ እኛን አይመለከትም በማለት በይፋ ተናግሮ የወያኔ ቅጥረኛነቱን እንደ ካሳ ተክለ ብርሃን አረጋግጧል፡፡ አቶ በላይነህ ቢሮውን ጀግኖች አምባ መሽጎ የባንዳ ሥራ መሥራቱን እንዲያቆም ከደብረ ታቦር የተላከው መልእክት አጽንዖት ይሠጣል፡፡

በተጨማሪም ሰጠኝ አሰፋ የተባለ በደብረ ታቦር ፖሊስ የነበረ፣ መቶ አለቃ ፈንቴ እንዲሁም ተሻገር መንግሥቴ የተባለ የደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ ሾፌር የሆኑ ግለሰቦች በስለላ ሥራ የደብረ ታቦር ዐማራ ወጣቶችን በመሠለል የተሠማሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡ እነዚህን ግለሰቦች ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲጠነቀቁ፣ ቤተሰቦቻቸውም እንዲመክራቸው ብዙ የዐማራ ወጣቶች እየጠየቁ ነው፡፡

(የግለሰቦቹ ፎቶ ታች ቀርቧል)

ይህ በዚህ እንዳለ በሁለቱም ከተማዎች የሰላማዊ ሰልፉ የሚያስፈልጉ መሰናዶዎች ሁሉ በመጠናቀቅ ላይ ናቸው፡፡

3. ከጋይንት፣ ከወልዲያ፣ ደሴ፣ ደብረ ብርሃን፣ መራቤቴና ሞጣ ሰላማዊ ሰልፍ የማስተባበር ጥረት እንዳለ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ ደብረ ብርሃን ከተማ አንድ ወጣት የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄን በማንሳቱ ምክንያት ባለፈው ሳምንት መገደሉ የሚታወስ ሲሆን የዐማራ ሕዝብ ከየትኛውም ቦታ አገዛዙ በማንነቱ የሚያደርስበትን በደል እየተቃወመ ይገኛል፡፡

በእነዚህና በሌሎች ከተሞች የሚኖረውን እንቅስቃሴ በአካባቢው ያላችሁ የዐማራ ቁርጠኛ ወጣቶች መረጃ በማቀበልና በማስተባበር ኃላፊነታችሁን ተወጡ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *