አቶ ካሳ ተክለ ብርሀን ወልቃይት ወደ ትግሬ ክልል መካለሉ ትክክል ነው ብለው ትንታኔ ሰጡ !

አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን ወልቃይት ወደ ትግራይ ክልል መካለሉ ትክክል ነዉ ብሎ ትንታኔ ሰጠ።ንግግሩ በማር የተለወሰ መርዝ ነዉ።አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን ይህን የታሪክ ክህደት የፈፀመው አለቆቹን ወያኔዎችን ለማስደሰት ነዉ።አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን የበግ ለምድ የለበሰ አስመሳይ የተኩላ ባህታዊ ነዉ።ወልቃይት ህዝቡም አማራ መሬቱም ያማራ እንደሆነ ሀገር ያወቀዉ ፀሃይ የሞቀዉ ዘመን የማይሽረዉ እዉነት ነዉ።በተጨማሪም ይሄ ካሳ ተክለ ብርሃን የሚባል የብአዴን ካድሬ ዋግን ጠቅሎ ለትግራይ ለመስጠት የአፄ ካሌብ ልጆችና የአሸንዳ ሻደይ ባህል ከአማራዉ ሳይሆን ከትግሬዎች ጋር ያቀራርበናል የሚል አቋም ይዞ መንቀሳቀስ ጀምሯል የሚባል ወሬ ሰምቻለሁ።ለማንኛዉም ጎበዝ ብአዴኖችን ማመን ቀብሮ ነዉ፤ብአዴንን ማመን ውሃን እንደመጨበጥ ነው።ከመነሻዉ ጀምሮ ብአዴን የአማራን ህዝብ መብትና ጥቅም ለማስከበር የቆመ ድርጅት ሳይሆን የወያኔ ጉዳይ አስፈፃሚ ነው።ቀጥኘ ቢያየኝ ጅማት ለመነኝ አለ ያገሬ ሰዉ።ሰፊዉ የአማራ ህዝብ ጥቅሙን፣ነፃነቱንና መብቱን ለማስከበር በአንድነት ጠንክሮ መታገል አለበት።ጎበዝ በያለህበት የድርሻህን ለመወጣት ተነሳ፤በያለህበት ተደራጅ ተነጋገር ድር ቢያበር አንበሳ ያስር።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *