ዶክተሮች በሀብታሙ አያሌዉ ጉዳይ የመጨረሻ ዉሳኔ አሳለፉ ፡፡

ሰበር ዜና

ዶክተሮች በሀብታሙ አያሌዉ ጉዳይ የመጨረሻ
ዉሳኔ አሳለፉ ፡፡
================================

የካዲስኮ ሆስፒታል የቦርድ አባላት ከትላንት በስቲያ ቀደም ሲል በጀነራል ሰርጂኑ በዶክተር አብርሃም አስናቀ ተፈርሞ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተላከዉን የህክምና ማስረጃ አፀደቁ፡፡

በተያያዘ የሆስፒታሉ ዶክተሮች “ከበሽታዉ መወሳሰብ አንፃር ለከፋ አደጋ ከመጋለጡ በፊት በሀገር ዉስጥ ወደ እማይገኘዉ ኮሎ ሬክታል ሴንተር በመሄድ አስቸኳይ ቀዶ ህክምና እንዲደረግለት ወስነን ሳለ ህመምተኛዉን በሆስፒታላችን ማቆየት አንችልም” በማለት በትላንትናዉ እለት እንዲወጣ ትእዛዝ ሰጥተዉ ነበረ፡ ይሁን እንጂ ሀብታሙን ባለበት ሁኔታ ወደ መኖርያ ቤቱ ማስገባት የ4አመት ህፃን ልጁን ማሳቀቅ ስለሚሆን እና የግድ የህክምና ደጋፍ ስለሚያስፈልገዉ ተጨነቅን፡፡ ሌላ ሆስፒታል እንዳንሄድ የጠየቅናቸዉ ሁሉ “ምንም መርዳት የማንችለዉን ህመምተኛ ያዉም ቦርድ ዉሳኔ ሰጥቶበት ልናስተኛዉ አንችልም አሉን፡፡” ትላንት በጣም ታሞብን ስለነበረ ሆስፒታሉን ተማፅነን አደርን፡፡ ያም ቢሆን ዶክተሮቹ ለትላንትናዉ ሌሊት ሀላፊነት አንወስድም ብለዉ ተማፅኖአችን ለማደር ብቻ ነበረ፡፡ ዛሬ ግን እንድንወጣ ስለተገደድን የግለሰብ ቤት ተከራይተን ፍቃደኛ በሆኑ የግል ሀኪሞች ስቃይ ማስታገሻ እንዲሰጠዉ እያደረግን ነዉ፡፡ ያ ሀገር የማይበቃዉ የህዝብ ልጅ እንዲህ ሆኖ ማየት በጅጉ ያማል፡፡ ቀጣዩን ተከታትዬ አሳውቃለሁ…

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *