ሰበር ዜና። የጎንደር ከተማ ህዝብ ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።

ሰበር ዜና
ተከታታይ መረጃ

የጎንደር ከተማ ህዝብ ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።

ፌደራል ፖሊሶችና መከላከያዎች ባንኮችንና የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ብቻ እየጠበቁ ነው። የህወሃት የንግድ ቤቶችና ሰላም ባስ አውቶቡስ ተቃጥሏል። ወጣቱ አካባቢውን በድንጋይ እየዘጋ ፖሊሶች መተላለፊያ እንዳያገኙ እያደረገ ነው። ጎንደር ከዚህ ቀደም ባልታዬ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተናጠች ነው።
የወልቃይት ህዝብ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ለማገዝ በጉዞ ላይ መሆኑም ተሰምቷል። ወታደሮች ጥግ ጥግ ይዘው አካባቢውን እየቃኙ ነው። የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።
እስካሁን ባለን መረጃ 7 ሰዎች እና 4 የፌደራል ፖሊሶች ተገድለዋል። በመንግስት በኩል የተሰጠ መግለጫ ባለመኖሩ የሟቾችን ቁጥር ለማወቅ አልተቻለም። ኢሳት የኮሚቴው አባላትንና ነዋሪዎችን አነጋግሯል። ሁሉም በአንድ ድምጽ ጎንደር ታይቶ በማይታወቅ ተቃውሞ እየተናጠች ነው ይላሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *