ቴዲ አፍሮን እንወደዋለን ሃይሌን ግን ኣናውቀውም ( ሄኖክ የሺጥላ )

ቴዲ አፍሮን እንወደዋለን ሃይሌን ግን ኣናውቀውም ( ሄኖክ የሺጥላ )
ህውሃት በኦሮሚያ የተነሳውን አመፅ ለማብረድ ፥ ብሎም የአክራሪ ኦሮሞነትን ራስ ለመምታት ለጊዜው ቂሜን ሊያዋልዱ ይችላሉ ያለችውን ነገር እያደረገች ትገኛለች ።
ከነዚህ ውስጥ አንዱ የህወሓት ተላላኪው ሃይሌ ገ/ስላሴ ለጀነራል ጀጋማ ኬሎ የፋሲካ ያክፋይ ይዞ መሄዱና ይህም በ ኢቲቪ ( ኢቢሲ) መዘገቡ ነው ። ለቴዎድሮስ ካሳሁን ከፍተኛ ጥላቻ ያለው ይሄው ስርዓት ኦሮሞውችን ኩም ያደርግልኛል ብሎ ስላሰበ የቴዲ ኣፍሮ « የወደ ፍቅር ጉዞ » ዝግጅት በ በ ኢቲቪ ( ኢቢሲ) እንዲተላለፍ ኣድርጓል ። ነገ ደሞ የአጤ ሚኒሊክን ሃውልት የብር ቀለም እንቀባ ብለው ሲነሱ ማየታችን የማይቀር ነው ። ለምሳሌ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞ ባነሱበት ወቅት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች የጥምቀትን በዓል ምንጣፍ ኣንጥፈው እንዲያከብሩ መንገዱን እንዳመቻቹ እናውቃለን ። ይህ ፍቃዳቸው ከበጎ ጭንቅላት የመነጨ እንዳልነበረ ለማወቅ ከወራት በፊት ዋልድባን ለማፍረስ ደፋ ቀና ይሉ እንደነበር ስናስታውስም ጭምር ነው ። ህዝቡ እንዲረዳልኝ የምፈልገው ነገር ግን ፥ በኦሮሚያ የተነሳውን ግርግር ኣናቱን ለማለት እየተደረገ ያለውን ነገር እንድትረዱልኝ ነው። ቴዲ ኣፍሮን እንወደዋለን ፥ ሃይሌን ግን ኣናውቀውም !

የግርጌ ማስታወሻ
በቅርቡ ሃይሌ የኢትዮጵያ ህዝብ ምግብ እንጂ ያጫጨው የዲሞክራሲ ( የነፃነት ) እጦት ኣይደለም ብሎ ነበር። ጀጋማ ኬሎ ደሞ ለነፃነታችን የተዋደቁ ትልቅ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ታዲያ ሃይሌ እሳቸው ቤት ምን ይሰራል ?

ኢትዮጵያ ትቅደም ( ሄኖክ የሺጥላ !!!)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *