በዘውዲቱ ሆስፒታል እንቅርት ለማውጣት ሆድ የቀደዱት ሐኪም ከስራና ከደሞዝ ታገዱ ።

እንቅርቷን ሆዷ ላይ ኣጡት ( ሄኖክ የሺጥላ )

«በዘውዲቱ ሆስፒታል እንቅርት ለማውጣት ሆድ የቀደዱት ሐኪም ከስራና ከደሞዝ ታገዱ ። » እኔ በ ዶክተሩ ላይ አልፈርድም ። ምግብ በልቶ የማያቅብ ህዝብ ሆዱ እና እንቅርቱ እኩል ሆኖ ለመለየት ተቸግረው ይሆናል ። እዚህ አማሪካ ቢሆን « ይቺ ጠጋ ጠጋ ኩላሊት ለመስረቅ ነው » ተብሎ ዶፍተርዬ ስንት መከራውን ባየ። ግን እድለኛ ዶክተር ነው ። የተሳሳተው ኢትዮጵያ ፥ የተቀጣው « ከስራና ከደሞዝ መታገድ ብቻ!»

በነገራችን ላይ ወደፊት እንቅርት የት ጋ እንዳለ ለማሳየት እንደ ጠላ ቤት አንገታችን ላይ ጣሳ ማንጠልጠል ይኖርብን ይሆን ? ወይስ በዚህ በኩል ታጠፍ የሚል ቀስት ኣንገታችን ላይ ልንነቀስ ?

አየህ ሀገር ሲያረሥጅ ፥ ሽበትም ሲያወጣ
እንቅርትን አንጀት ላይ የሚፈልግ ዶክተር
ኣሰልጥኖ ኣመጣ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *