ለመሆኑ “ከበባ” ተደርጎ ነበር? ነው ዜናውን ከኪሳችሁ አውጥታችሁ ነው የሰራችሁት? ለማንኛውም የ”ከበባውን” ውጤት እየጠበቅን ነው!!

ከደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ዘልቀው በገቡ ወንበዴዎች ከሁለት መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ከተገደሉና በርካታ ሴቶች እና ህጻናት ታግተው በተወሰዱ ማግስት “መከላከያ ሰራዊታችን ወደ ደቡብ ሱዳን በመግባት የታገቱትን ህጻናት ለማስለቀቅ ከበባ አድርጎ ይገኛል” የሚል ዜና ከሂሊኮፕተር ላይ በመዝለል ላይ ባሉ ወታደሮች ፎቶግራፎች ተደግፎ በወያኔ ካድሬዎች አማካኝነት ሲሰራጭ መክረሙ ይታወቃል። ይሁንና የ”ከበባው” ዜና ከተሰራጫ ቀናት ያለፉ ቢሆንም “ከበባውን” በተመለከተ ጌታቸው ረዳም ሆነ በፌስቡክ ሲጨፍሩና ሲያስጨፍሩ የነበሩ የወያኔ ካድሬዎች የ”ከበባውን” ውጤት ከመግለጽ የተቆጠቡበት ሁኔታ ነው ያለው።

ለመሆኑ “ከበባ” ተደርጎ ነበር? ነው ዜናውን ከኪሳችሁ አውጥታችሁ ነው የሰራችሁት? ለማንኛውም የ”ከበባውን” ውጤት እየጠበቅን ነው ያለነውና አፕዴት (Update) አድርጉን። ይህንን ዜና ያሰራጫችሁ ቡድኖች ጉዳዩን ረስታችሁት ከሆነ ለማስታወስ ያህል ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *