ስደተኞቹ ኢትዮጵያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉ በኋላ በጋምቤላ ከተማ መረጋጋት ጠፍቷል።

በጋምቤላ ያለው ሁኔታ
-ስደተኞቹ ኢትዮጵያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉ በኋላ በጋምቤላ ከተማ መረጋጋት ጠፍቷል። ለሁለት ቀናት ህዝቡ ተቆጥቶ እርምጃ ሊወስድ ሲዘጋጅ በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ተከልክሏል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ስደተኞቹ ታጥቀዋል። ይህ ደግሞ ህዝቡን ስጋት ውስጥ ከቶታል። በማንኛውም ጊዜ ስደተኞቹ ጥቃት መሰንዘራቸው አይቀርም። ስደተኛ መሳሪያ የታጠቀባት ብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ ትሆን?
-ለጊዜው ስደተኞቹም ወደ ከተማ የጋምቤላ ነዋሪዎችም ወደ ካምፕ እንዳይሄዱ መሃል ኬላ ተበጅቶ እየተጠበቀ ነው። ስደተኞቹ በሰው ሀገር የፈለጋቸውን እያደረጉ ነው። ምግብ የሚያቀርቡላቸውን፡ ህክምና የሚሰጧቸውን ኢትዮጵያውያንን ገድለዋል። ገሚሶቹ በየጫካው ተደብቀዋል። የውጭ የግረሰናይ ድርጅት ከካምፑ ጠቅልሎ ወጥቷል። አሁን ስጋቱ እኚህ ስደተኞች ከ3 ቀናት በኋላ ምግባቸው ያልቃል። ሲርባቸው ወደ ጋምቤላ ከተማ መምጣታቸው የማይቀር ነው። ሲመጡ የታጠቁትን መሳሪያ ይዘው ነው።…… ጋምቤላ ሆይ!!! ከክፉ ይጠብቅሽ! !ከመሳይ መኮንን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *