እራሳችንን ማታለሉ ይብቃን!

እራሳችንን ማታለሉ ይብቃን!! ኢትዮጵያዊያን ጋምቤላ ላይ በሱዳናዊያን መጭፍጨፋቸው ቢያንገበግበኝም ይበልጥ የሚያመኝ እንደተለመደው ‘ሪፕ’ ብለን ቁጭታችንን በመግለጽ የቡና እና የድራፍት ቤት ማጣጫ ወሬ ሆኖ መቅረቱ ነው። በወልቃይትም የተደረገው እና እየተደረገ ያለው ጭፍጨፋ ከጋምቤላ የሚለየው ጨፍጫፊዎቹ በግልጽ የኢትዮጵያን የመንግስት ስልጣን በኛ ወሬኛነት ምክንያት እስዛሬ ድረስ የያዙት ዘረኛ የባንዳ ልጆች መሆናቸው ነው። እነዚህ ሰዎች ከቡናቤት እና ከመንደር ብሎም ከፌስቡክ ወሬ የዘለለ ቁምነገር ስንሰራ ስላላዩን በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይሆን በየቤታችን ለመንገስ እስከማስገደ ደርሰዋል። ጋምቤላዎች ትናንት በሱዳናዊያን ሽፍቶች ተጨፈጨፉ እንጅ ከትናንት ወዲያ በኢትዮጵያ ‘መንግስት’ ታርደዋል።ተጨፍጭፈዋል። ይህ የምታዩት ፎቶ የዛሬ ሁለት ዓመት ጋምቤላ ላይ መሬታቸውን አናስነካም በማለታቸው እንደ ባዕድ ጠላት በሃገራቸው ላይ ታፍነው የነበሩ ሰዎች ናቸው።ይኑሩ አይኑሩ የሚታወቅ ነገር የለም።የኢትዮጵያ ጦር የት ሄዶ ነው የጋምቤላ ሰዎች የተጨፈጨፉት ለምትሉ የዋሆች የኢትዮጵያ የሚባለው የወያኔ ሰራዊት ከፊሉ እዚያው ጋምቤላ ውስጥ ነው። ዓላማው ግን ሱዳናዊያን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ሲያልፉ መከላከል ሳይሆን በዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ከመሬታቸው ማፈናቀል፣ማሳደድ እና አለቆቻቸው የሚዘርፉትን ሃብት ችግር ሳይገጥመው ወደመሃል አገር እና ደቡብ ሱዳን እንዲጓጓዝ መከላከል ነው። እስቲ ፎቶውን እዩት! እነዚህ የጋምቤላ ሰዎች ክላሽ በያዙ ወታደሮች ተከበው የምታዩቸው በሱዳን ወታደሮች ይመስላችኋል? “ከቅዱስ መሀሉ”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *