ወይ ፍረድ ወይ ውረድ እንበል!

እ.አ.አ 02/01/2016 ዓ.ም በጋንቤላ የተከስተው ግጭት በርካታ አኝዋክ በኑዌር ተገለዋል ። ገጀራ የያዙ በርካታ ስዎች በመኪና የተጫኑ የመንግስት ሰራዊቶችን አልፈው ሲጓዙም አይተናል ፤ አንድ የንዌር ተወላጅ እስር ቤት ውስጥ ገብቶ ብዙ ሰው ገሏል ፣ የደቡብ ሱዳን ባንዲራም እንደተውለበለበ ስምተናል ( ለአንድ ደቂቃም ቢሆን እንዴት የሌላ አገር ባንዲራ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ይውለበለባል ? ይህ ገሎ መፎከር እና ምን ይመጣል ማለት አይደለም ? ንቀትስ አይደለም ? ) ይህ ሁሉ ሆኖ ምንም መፍትሄ ሳይመጣ እና ሳይሰማ እነሆ ዛሬ ደግሞ ጉድ ሰማን ።

140 ሰዎች ከውጭ በገቡ ታጣቂዎች እንደተገደሉ ሰማን ። ፀረ ሰላሞችን አጥብቆ የሚከታተለው ተወዳዳሪ የሌለው ደህንነት ግን ምን ደረሰ ? 140 ሰው ሲገደል የት ነበር ? እኔ በበኩሌ ይህ ሁሉ ወያኔ የዘር ማጥፉት ዘመቻ እያጧጧፈ እንደሚገኝ ነው የማምነው ። ግን እስከመቼ እኛም እንደዛች የገጠር ሴት …..

የገደለን መግደል እንዳስቆምክ እናውቃለን
ይቅር እንዳንል እኛ አንተን አይደለን
ወይ ፍረድ ወይ ውረድ እንጓዳብሃለን …..እንበል??
መንበረ ካሳዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *