ታላቅ ሃገራዊ አማራዊ ንቅናቂ ለማድረግ ብንዘጋጅ!

ከአፄ አንድነት ወደ አማራ ስርወ ስሜት ( ሄኖክ የሺጥላ )

ሓዋሪያው ጳውሎስ ( የሃዋሪያት ስራ ምዕራፍ 26 ላይ እንዲህ ይላል )

«9፤እኔም፡ራሴ፡የናዝሬቱን፡የኢየሱስን፡ስም፡የሚቃወም፡እጅግ፡ነገር፡ኣደርግ፡ዘንድ፡እንዲገባኝ፡ይመስለኝ፡ ነበር።
10፤ይህንም፡ደግሞ፡በኢየሩሳሌም፡አደረግኹት፤ከካህናት፡አለቃዎችም፡ሥልጣን፡ተቀብዬ፡እኔ፡ከቅዱሳን፡ብዙዎ ችን፡በወህኒ፡አሳሰርዃቸው፥ሲገድሏቸውም፡ዐብሬ፡ተቸኹ።
11፤በምኵራብም፡ዅሉ፡ብዙ፡ጊዜ፡እየቀጣኹ፡ይሰድቡት፡ዘንድ፡ግድ፡አልዃቸው፤ያለልክ፡ስቈጣባቸውም፡እስከውጭ ፡አገር፡ከተማዎች፡ድረስ፡እንኳ፡አሳድድ፡ነበር።» ይላል

ኣዎ አማራ ሲሉኝ ኢትዮጵያ እያልኩ በአማራነት የቆሙ ወገኖቼ ላይ ኣላግጥ ነበር ፥ ትንሽ ሆናችሁ እያልኩ ድርጊታቸውን እከላከል ነበር ፥ ኣካሄዳቸውን እተች ነበር ፥ ከትግሬ ጋ ኣብሬ ፥ ከዘረኛው ኦነግ ጋ ደብዬ ወገኖቼን በዝምታ ኣስፈጅቻለሁ ። እውነቱን ባለመናገር ፥ ከራሴ በመደበቅ ፥ ኣንድነት በተባለ ስሜት ወገኖቼን ኣስጨርሻቸዋለሁ ። በዝምታ !

ዛሬ በኢትዮጵያዊነት ስሜት ከሰከርንበት እና ከከሰርንበት ማጀት ፥ ወደ አማራዊ ማንነት ለመገስገስ ግራ ቀኙን ኣይተን ያንድ ሺ እርምጃውን ኣንድ ብለን ጀምረናል ። ይሰማል?

«ከኢትዮጵያዊነት በታች መጥበብ ኣይችልም ስሜቴ
ኣርበ ሰፊ ነው ቆዳዬ ማደሪያ የሆነው ለትብቴ» ብለው የገጠሙ ነብሶች ያለ ኣንዳች መከፋት ፥ ያለ ኣንዳች ምክንያት የአማራነትን ጎዳናን ይመርጡ ይሆን ?
ምን መሰለህ ፥ ከቁስል ጋ ነው የኖርነው ! ስናስታምም ! ይገባኻል ? ስናስታምም ነው የኖርነው ነው የምልህ ! ትግሬ ስናስታምም ! ኦነግ ስናስታምም ! ኣንድ ጫት ያሰከረው ፥ ደም የጠማው ሜንጨኛ ስናስታምም ! ስናስታምም ኖርን ወንድሜ!
ኣየህ ተገድለን እንደ ገዳይ ፥ ተበድለን እንደ በዳይ ፥ ተዘርፈን እንደዘራፊ ፥ታርደን እንደ ኣራጅ ታየን ፥ ሃምሳ ሰይጣናም ፥ ሃምሳ ቀለም ያለው ባንዲራ ይዞ ሲዝትብን ፥ በቆንጨራ ነው በገጀራ ፥ በሜንጫ ነው በጡጫ እያለ ምድረ ኣብሿም ሲዘብትብን ፥ ኢትዮጵያን ብለን ደጅ ጠናን ፥ ሃገራችንን ብለን ኣንገታችን በመጎንበስ ጎበጠ ። ኣዎ ስንማጠን ፥ ስንለምን ፥ ሃገር እንዳትፈርስ ብለን ስለ እኩልነት ስናወራ ፥ ስለ ፍቅር ስናወራ ፥ ስለ ኣንድነት ስንሰብክ ኖርን ፥ ስለ ወንድማማችንችት ስንለፈልፍ ፥ ሽራፊ ዘር እየቆጠርን ፥ ደምህ ደሜ ነው እያልን ስንወዛገብ ፥ የቆምክበት ምድር ከዳችህ ። ግራ ቀኝ የቆሙት ፥ ያቆሙህ ወገኖችህ በማምከኛ ፥ በኤድስ ፥ በረሃብ ፥ በበደኖ ገደል ፥ በትግሬ ጥይት እንዳይሆን እንዳይሆን ሆነው ኣለቁ ። ታዲያ ዛሬም ቁሜ ስለ ኣንድነት ላውራ? ዛሬም የህዝቦች እኩልነት ልበል ? ዛሬም ፍቅር ያሸንፋል ብዬ ልስበክ ? ፍቅር ቢያሸንፍ ኖሮ በየ ስርጡ ፥ በየ ተራራው ፥ በየ ጫካው ፥ በየ ጨለማው የፈሰሰው የኣማራ ደም የፍቅር ጅረት ሆኖ ባሸነፈ ነበር ! ፍቅር ቢያሸንፍ ኖሮ የኣስራት ህይወት የስንት ሃጢያተኛን ነብስ ባስነሳ ነበር። ፍቅር ኣያሸንፍም! ጉልበት ነው የሚያሸንፈው ። ጉልበተኛ ሁን ! ኣቅም ይኑርህ ! ጥርስህ መዘንጠል ፥ ክንድህ መገንጠል ሲችል ስለ ፍቅር ኣውራ ! ይህ ለኣማራዊ ማንነቴ የማላብሰው ኣቅም ነው !

ታላቅ ሃገራዊ አማራዊ ንቅናቂ ለማድረግ ብንዘጋጅ ምን ትላላችሁ ? አቅሙ ኣለን፥ እውቀቱ ኣለን ፥ እልሁ ኣለን ፥ ደሙ ኣለን ፥ ታሪኩ ኣለን ፥ በዚያ ላ ደሞ እኛም ኣለን ! ኣልሞትንም ! ይህ ጥሪ ሁሉንም የኣማራ ልጅ ይመለከታል ። አማራ የበይ ተመልካች የሆነበት ብቻ ሳይሆን በአማራ ደም ተንሳፈው ቤተ መንግስት መግባት የሚፈልጉ ጭልፊቶችም ይህንን ኣቋማችንን ይረዱልን ። መዞር የለም! የዞረ የጨው ሃውልት ነው የሚሆነው!
ሄኖክ የሺጥላ !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *