የትግሬው አፈ ንጉስ ደጃስማች መለስ ዜናዊ

የትግሬው ኣፈ ንጉስ ደጃዝማች መለስ ዜናዊ ( ሄኖክ የሺጥላ )

የትግሬው «ኣፈ ንጉስ» ንጉስ ደጃዝማች መለስ ዜናዊ ካባታቸው ከዜናዊ ኣስረስ ፥ ካያታቸው ከሹምባሽ ኣስረስ ፥ በኣድዋ ክፍለ ሃገር ባንዲት ትንሽ መንደር ለመወለድ ሞከሩ።
በልጅነታቸው እጅግ ኣስቀያሚ ስለነበሩ የቅርብ ዘመዶች እንኳ እንደ ልጅ ሳያቅፏቸው እንዳደጉ የቅርብ ጎረቤቶቻቸው ያወራሉ ። ደጃዝማች መለስ እድሜያቸው ለኣቅመ ተንኮል እንደደረሰ ባንድ ከመንደራቸው ከሚገኝ የኳስ ሜዳ በመሄድ ልጆች ኳስ እንዳይጫወቱ እንቅፋት የመሆኑን ስራ ይሰሩ ጀመሩ። ባካባቢው ኣልፎ ኣልፎ የሚታዩ እርግቦችን በድንጋይ በማባረር ፥ ከብቶችን ወደ ገደል በመምራት ፥ቁልቋል እና ኣጋሞችን በማውደም ፥ ህፃናትን በማጋጨት ተንኮላቸውን ኣዳበሩት ። ሗላ ላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጀነራል ዊንጌት መከታተል ሲጀምሩ ፥ተንኮላቸውን ፈር በማስያዝ እና ሃገራዊ መልክ በመስጠት የብሄር ቁማራቸውን በወጣትነት እድሜያቸው ሃ ብለው ጀመሩ። የኣያታቸውን የሹምባሽ ኣስረስ ፈለግ በመከተል ፥ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ ጥርሳቸውን ነክሰው ተነሱ ። ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሲሉም ወደ ደደቢት በርሃ ተሰደዱ ። በትግራይ ተራሮች ላይ በትግሉ ውስጥ በቆዩባቸው ኣመታቶች ፥ የትግራይ ገበሬን በማታለል ወደ በርሃ እንዲገባ ኣደረጉት ፥ ኣብዛኛውን የትግል ኣጋሮቻቸውን በርሃ ላይ እየገደሉ ደርግ ራሱን ኣሸንፎላቸው ከተማ ገቡ ። የኤርትራ መገንጠል ላይ ጉልህ ሚና ተጫወቱ ፥ ኣሰብን ኣሳልፈው ሰጡ ፥ ኢትዮጵያን ወደ ኣልባ ኣደረጉ ፥ በብዙ ሺዎች ( ምናልባት ሚሊዮን ) የሚቆጠሩ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን በኦነግ ስም ኣሰሩ ፥ ገደሉ ፥ ደብዛቸውን ኣጠፉ ፥ ኣሁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኣማራ ብሄር ተወላጆችን ኣሰሩም ፥ ገደሉም ። ለሱዳን የኢትዮጵያ ክፍል የሆነውን እና በጎንደር ክፍለ ሃገር የሚገኝ ሰፊ መሬት ተቆርጦ የሚሰጥበትን ካርታ ኣረቀቁ ፥ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች በኣንድነት ሊኖሩ የማይችሉበትን የብሄር ፖለቲካ ጠነሱሱ ። የትግራይን የበላይነት ለማረጋገጥ የሚያስችለውን ማንኛውም ኣይነት ፥ ግፍም ሆነ ተንኮል ፥ ግድያም ሆነ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ኣካሄዱ ። ለዚህ ወሰን የሌለው ግፍና ጭካኔያቸው ኣምላክ በነቀርሳ ደማቸውን ኣበሰበሰልን ፥ ቀጥሎም ገደለለን ። ሰላም ልናገኝ ነው ብለን ተስፋ ስናደርግ ፥ እኝህ ሰው ከመቃብር ባለ ራዕይ ሆነው ብቅ ኣሉ ። በመጀመሪያው ቀን በሞተ ህዝብ መኀል ሞትን ድል ኣድርገው ተነሱ ። እሳቸው ግን እንደ ክርስቶስ ከኣባታቸው ከዜናዊ ኣስረስ ጎን ሄደው ኣልተቀመጡም ። ይልቁንም በኦሮሚያ ብዙ ሺ ሄክታር መሬት ገዝተው « የኔ ፋውንዴሽን » ብለው በሙት መንፈስ እያዘዙ ፥ ይገዙ ጀመር ። ከክርስቶስ በኋላ ሞተው ከክርስቶስ በፊት ወደ ምድር ተመልሰው የመጡ ድንቅ ሰው ! ይህ ፍጥነታቸው ያስቆጣቸው የኦሮሚያ እና ኣካባቢው ነዋሪዎች « በመሰሪው መሲህ ላይ ተነሱ » ፥ እንደ ክርስቶስ ደሳለኝ በሚባል የኣህያ ውርንጭላ ከተማ ገብተው ህዝቡን ኣህያ ኣድርገው የሞቱት እኝህ « ነበልባል ነብይ » ዘመናት የሚሻገር ኣፍቃሪ ማግኘት ኣልቻሉም ! ይልቁንም ህዝቡ «ይህንን ባለ ራዕይ ኣንሳው
ከላዬ ላይ» ይል ጀመር ።

የጀግና ቀብር የተቀበሩት መለስ ዜናዊ ኣስረስ ፥ ከሞቱ ኣራት ኣመት ሳይሆናቸው ፎቷቸው በኣደባባይ ይቃጠል ጀመር ። ወደፊት ባዶ ሳጥን ከቀበሩበት ስላሴ ቤ/ክርስቲያንም ይሁን ፥ እውነተኛ ኣስክሬናቸው ካረፈበት ትግራይ ወጥቶ ይቃጠል ይሆን ? ማን ያውቃል ፥ የግዜ ጉልበት የፍርድ ሚስጥሩ ላይም ኣይዶል ያለው!

ቀጣዩን ውሳኔ ለትውልድ ትተን ፥ ትውልዱ የደረሰበትን በደል ያውቅ ዘንድ እውነቱን መናገሩን ብንቀጥልስ ? ያወቀ እና የነቃ ትውልድ እንኳን ሬሳ ፥ የታጠቀ ወታደር እንደሚያቃጥል ኣይተናልና!

ኣሪፍ እሁድ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *