የጣና ሞገድ የሚል ያሜ ያለው የባህር ዳር እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾቹ በመቀሌ ደጋፊዎች መደብደባቸው ሳይንሳቸው ክለባቸው የ450ሺ ብር ተቀጣ!

ኢሳት (ግንቦት 17 ፥ 2009) ከመቀሌ አቻው ጋር ሲጫወት በትግራይ ደጋፊዎች ተደብድቦ ወደ አማራ ክልል የተመለሰው የባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጥፋተኛ ተብሎ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቅጣት ተጣለበት። የባህር ዳር ከነማ ክለብ በረኛን ጨምሮ 4 ተጫዋቾች በቀይ ካርድ ተባርረው በ7ቱ ብቻ ወደ መቀሌ ሄዶ ደጋፊ በሌለበት ዝግ ስታዲየም ጨዋታው ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ ያለው 16 ደቂቃዎች ከመቀሌ አቻው ጋር ውድድር እንዲጨርስ ግዴታ ተጥሎበታል። 4ቱ ተጫዋቾቹ ለ3 ውድድሮች እንዳይጫወቱም እገዳ ተጥሎባቸዋል። የጣና ሞገድ የሚል ያሜ ያለው የባህር ዳር እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾቹ በመቀሌ ደጋፊዎች መደብደባቸው ሳይንሳቸው ክለባቸው የ450ሺ ብር ቅጣትም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተወስኖበታል። የመቀሌው ከነማ እግር ኳስ ክለብም 1 መቶ ሺ ብር ለይስሙላ ቅጣት እንደተጣለበትም ለማወቅ ተችሏል። የባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች በያዝነው ግንቦት መጀመሪያ ከመቀሌ ከነማ ክለብ አቻው ጋር ትግራይ ድረስ ሄደው ሲጫወቱ በብሄር ማንነት ላይ ያነጣጠረ ስድብ በደጋፊዎች መሰደባቸው አይዘነጋም። በተለይ በጨዋታው ጊዜ የተጎዳው የባህር ዳር ተጫዋች ከሜዳ ሲወጣ በወጌሻዎች ተወርውሮ ሲጣል በተፈጠረ ግጭት ጨዋታው አንድ ለአንድ በሆነ ውጤት ተቋርጦ ነበር። ተጨዋቾቹ ከመቀሌ እንዳይወጡ ታግደው እንደነበርም አይዘነጋም። ከዚህ በኋላ ጉዳዩ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ቴሌቪዥና በአማራ ቴሌቪዥኖች እንዳይዘገብ ከተወሰነ በኋላ በመቀሌ ከንቲባ አቶ ዳንዔል አሰፋ የተመራ የልዑካን ቡድን ባህር ዳር ድረስ መጥቶ ሚስጥራዊ ስብሰባ ከአማራ ክልል ባለስልጥናት ጋር ሲያደርግ እንደነበር ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያስረዳል። በመጨረሻም፣ የባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጥፋተኛ ተብሎ የገንዘብ ቅጣትና የተቋረጠውን ውድድር በ8 ተጫዋቾች ብቻ እንዲጨርስ፣ 450 ሺ ብርም እንዲከፍል ግዴታ ተጥሎበታል። የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ፣ (ኢሳት) የጨዋታውን በረብሻ መቋረጥ ተከትሎ የነበረውን ሂደት ሲዘግብ መቆየቱ ይታወሳል። ምን እንኳን ጥፋቱ የመቀሌው ክለው ነው ቢባልም፣ የባህርዳር እግር ኳስ ክለብ የችግሩ መንስዔል ተደርጎ ፖለቲካዊ ውሳኔ ሊሰጥ እንደሚችል መግለጻችንም አይዘነጋም።

የጎንደር ተወላጅ ወታደር በርካታ መኮንኖችን ገድሎ በመጨረሻም ራሱን አጥፍቷል።

ግንቦት ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር በምትገኘው ጎዴ ከተማ የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት አባል የሆነው የጎንደር ተወላጅ ወታደር በርካታ መኮንኖችን ገድሎ በመጨረሻም ራሱን አጥፍቷል። ወታደሩ ድርጊቱን የፈጸመው በአየር ሃይል የምህንድስና ትምህርት ተምሮ ጎዴ በእግረኛ ወታደርነት መመደቡን ተከትሎ ነው። ምንጮች እንደገለጹት ፣ ወታደሩ ያለምንም ምክንያት ወደ ጎዴ ተወስዶ በእግረኛ ወታደር አባልነት እንዲሰራ የተመደበ ሲሆን፣ ይህንን ውሳኔም ሲቃወም ቆይቷል። “ ከአየር ሃይል ምድቡ ተነስቶ ለምን በእግረኛ ወታደርነት እንዲሰራ እንደተመደበ መልስ እንዲሰጠው ባለስልጣኖችን በተደጋጋሚ ጠይቆ ምንም መልስ ያላገኘው ወታደር፣ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ጊዜ ሲጠብቅ እንደነበር ምንጮች ይገልጻሉ። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የጦር መኮንኖች ከስብሰባ ሲወጡ ጠብቆና አዘናግቶ እርምጃ መውሰዱን የሚናገሩት ምንጮች፣ ከ10 በላይ የጦር መኮንኖች ተገድለዋል ብለዋል። አካባቢው ወዲያውኑ በመዘጋጋቱ ትክክለኛውን የሟቾችን አሃዝ ለማወቅ ባይቻልም፣ የአካባቢው ምንጮች የሟቾች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑንና ፣ ወታደሩም ራሱን ማጥፋቱን ገልጸዋል። ሌሎች ምንጮች ግን ወታደሩ በጠባቂ ወታደር መገደሉንና ራሱን አለማጥፋቱን ይገልጻሉ። የወታደሩና የመኮንኖቹ አስከሬን እዛው ጎዴ ውስጥ መቀበሩንም ምንጮች ገልጸዋል። ወታደሩ በቅርቡ በአማራና በኦሮምያ ከነበረው ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ጋር ተገምግሞ ወደ ጎዴ በቅጣት መልክ መወሰዱም ታውቋል። በሌላ በኩል የምስራቅ እዝ ዋና አዛዥ ጄ/ል አብረሃ ወደ አዲስ አበባ የተወሰዱት ከሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት ጋር የፈጠሩት የጥቅም ግንኙነትን ተከትሎ ገምገማ በመደረጉ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ኢሳት ትናንት ባቀረበው ዘገባ ጄኔራሉ የወታደራዊ ዘመቻ ማስተባባሪያ ውስጥ መመደባቸውን የገለጸ ሲሆን፣ ቦታው የጀኔራሉን ሹመት ሳይሆን ውድቀት የሚያመለክት ነው በማለት ምንጮች ዘገባውን አርመዋል። ጄ/ል አብረሃ በአሁኑ ሰአት ይህ ነው በማይባል ሃላፊነት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው፣ እርሱ በሰራው የሙስና ወንጀል ልክ የሌሎች ብሄር ተወላጆች ቢሰሩት ኖሮ፣ ሰበብ ተፈልጎ ከስልጣን መባረር ብቻ ሳይሆን ክስ ይመሰረትባቸው እንደነበር ተናግረዋል። የጄ/ል አብረሃ ምክትል ሆነው ሲሰሩ የነበሩት የኦህዴድ አባሉ ብርጋዴር ጄኔራል ጌታቸው ጉዲናም እንዲሁ ከምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥነት ቦታቸው እንዲነሱ የተደረጉ ሲሆን፣ እሳቸውም ስልካቸው ላይ የኦህዴድ ባለስልጣናት ስልክ መገኘቱንና በኦሮምያ በተካሄደው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ተሳትፎ አድርገዋል የሚል ሂስ ተሰንዝሮባቸዋል። ጄኔራሉ የቀረበባቸውን ውንጀላ አስተባብለዋል። እርሳቸውን ከሃረር በማንሳት ወደ ሌላ ቦታ መመደባቸውም ታውቋል። በሌላ በኩል በባህርዳር የሚገኙ አንዳንድ የመከላከያ አባላት ፣”ህዝቡ እኛን እንደሰው አያየንም “ ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል። ወታደሮቹ ይህን አስተያየት የሰጡት፣ የግንቦት20ን በአል በማስመልከት ለወታደሮችና አዛዦች በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ ነው። ወኪሎቻችን በድምጽ ቀርጸው በላኩት ማስረጃ ላይ አንድ ወታደር “ በግንቦት 20 በአል ወታደሩ የአንበሳውን ድርሻ ይዟል ተብሎ ተነግሮናል፣ ነገር ግን ሲቪል ማህበረሰቡ ለወታደሩ ያለው አመለካከት የወረደ ነው።” የሚለው ወታደሩ፣ እኔ እዚህ ከተማ ላይ ያጋጠመኝ ልንገራችሁ ካለ በሁዋላ፣ “ አንድ ቦታ ላይ ሰው ተጣልቶ ስሄድ፣ አንዱ ‘ ሰውና ወታደር ተጣልቶ ነው’ ሲል ሰማሁት። ህዝቡ ለወታደሩ ያለው አመለካከት የዚህን ያክል ነው” ብሎአል። “የአምበሳውን ድርሻ ይዟል ካላችሁ ፣ ህዝቡ ስለኛ ያለውን አመለካከት እንዲቀይር የሚያደርግ ስራ ስሩ” ሲሉ ስብሰባውን ለሚመሩት ካድሬዎች ተናግሯል ። ሌላው አስተያየት ሰጪ መኮንን ደግሞ “ ባለፉት 2 እና 3 አመታት ብሄራዊ መግባባታን በተመለከተ እየቀነሰ መጥቷል። በተለያዩ ቦታዎች ግጭቶች እየታዩ ነው። አሁን ብሄራዊ መግባባት በምን ሁኔታ እንዳለ ቢነገረኝ” ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል። ሌላው ወታደር ደግሞ መልካም አስተዳደር የሚባለው ነገር የለም ይላል። “ሙስናን በተመለከተም አንድ ሰው የሙስናን ጉዳይ ሲያጋልጥ የበቀል እርምጃ እንደማይወሰድበት ምን ዋስትና አለ? እኔ የማውቀው አንድ በሙስና የተዘፈቀ ሰው፣ ከአንድ ቦታ ተነስቶ ወደ ሌላ ቦታ እንደሚሾም” ገልጾ፣ ሰዎች ሙስናን ሲያጋልጡ ዋስትና ሊሰጣቸው ይገባል ብሎአል። ስብሰባውን የመሩት ኮሎኔል ምንም እንኳ የመከላከያ አባላት ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ ነው ቢባልም፣ እርሳቸው ግን ራሳቸውን የኢህአዴግ አባል አድርገው ድርጅታቸውና መንግስት ሙስናን ለመዋጋት የወሰደውን እርምጃ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።

ግንቦት20 ለማክበር በላፎንቴን ስም የተጠራው ፈንጠዝያ ከባድ ፈተና ከፊቱ እንደሚጠብቀው ተገለፅ !

#ETHIOPIA | የህዝብ ነኝ ለማለት በሕዝብ ልጅ ላይ መንጠልጠል ህዝባዊ አያደርግም!!

ትንሽ አሻሮ ይዘህ ከቆሎ እንዲሉ የትም ከጠላቶቻችን ጋር ሲጨፍሩ ከርመው እዩን ለሚሉን አናይም ስሙን ለሚሉን አንሰማም እንላለን!!

የዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል በወያኔና በተባባሪዎቹ ላይ ተቃውሞ የምናሰማው መቃወምን ስለምንወድ ሳይሆን ለድምፅ አልባው ወገናችን ድምፅ ለመሆን ብለን እንጂ፤ በተለይ ኪነት ለነፃነት ትግልም ሆነ በባርነትም ለመቀጠል ትልቁን ሚና የሚጫወት መሆኑ ግልጽ ነው። ህዝብ ሲፈጅ ከህዝብ ጋር አብረው የቆሙ እንዳሉ ሁሉ በፋሺስት ሬሳ ላይ ጧፍ እያበሩ ያጀቡ ከያኒያን በርካቶች ናቸው፤ ታዲያ በነዚህ ላይ በየአካባቢው የምንገኝም ኢትዮጵያኖች ባገኘነው አጋጣሚ የተቃውሞ ድምፅ እናሰማለን ፤ እያሰማንም ነው፤ ይህም አልበቃ ብሎት ከአጋዚ መንጋዎች ጋር 40ኛ የቁም ተስካር ላይ ቅጠልያ ለብሶ የተንጎባለለው ታደለ ሮባ ሆነ የነ አላሙዲ አቀንቃኝ ደረጀ ደገፋ እንዲሁም ጆኒ ራጋ በዲሲ የተዘጋጀው የላፎንቴን ዝግጅት ላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ እስከ አርብ 05/26/17 ድረስ በአደባባይ ወጥተው ይቅርታ ሳይጠይቁ በመድረክ ላይ የሚወጡ ከሆነ ከፍተኛ ተቃውሞ የምናሰማ መሆናችንን እየገለጽን አዘጋጆቹም ይሄንን የሕዝብ ጥያቄ ቸል ብለው ቢያልፉ ለሚደርሰው ሁሉ ተጠያቂ እንደሆኑ ከወዲሁ እናሳስባለለን።

የዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል!

dcJointtaskforce@gmail.com

ሰበር ዜና ቴዎድሮስ አድሀኖም ላይ ከስብሰባው ጫን ያለ ተቃውሞ ተሰማ!!!

አሁን የደረሰን መረጃ

በጄኔቭ የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ምርጫ በመቃወም ከፍተኛ ሰለማዊ ሰልፍ እየተካሄድ ባለበት ሰአት ወደ ጉባኤ አዳራሹ የገቡት ታዋቂው አክቲቪስት አቶ ዘላለም ተሰማ፣ የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ስም ሲጠራ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው “ ዶ/ር ቴዎድሮስን ብትመርጡ ለሰብአዊ ዘር በሙሉ ሃፍረት ነው ፣ አፍሪካ አስቢ፣ ይህን ሰው መምረጥ ክስረት ነው የሚሉና ሌሎችንም ምክሮችና ጥያቄዎች በማቅረብ” ጉባኤው ለተወሰኑ ደቂቃዎች እንዲቋረጥ አድርገዋል። ከእርሳቸው ጋር የተደረገው ቃል ምልልስ ከጥቂት ደቂቃዎች በሁዋላ ይቀርባል።

አርበኞች ግንቦት 7 ቴድሮስ አድሃኖምን የሚያጋልጥ መረጃ ለቀቀ

አርበኞች ግንቦት 7 ቴድሮስ አድሃኖምን የሚያጋልጥ መረጃ ለቀቀ

የዓለም ጤና ጥበቃ ዳይሬክተርነት በህዝባችን ላይ የተፈጸመውን ወንጀል መሸፈኛ ሊሆን አይችልም!

አርበኞች ግንቦት 7

ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ድርጅትና እንደ መንግሥት በአገራችን ውስጥ እንዲተገበሩ በወጡ አፋኝ ፖሊሲዎችና በህዝባችን ላይ በተወሰዱ ፋሽስታዊ እርምጃዎች ሁሉ ወሳኝ ሚና ከነበራቸው ጥቂት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ቴዎድሮስ አድሃኖም አንዱ ነው።

ይህ ወንጀለኛ ግለሰብ የአምባገነኖች ስብስብ በሆነው የአፍሪካ ህብረት ሙሉ ድጋፍ አግኝቶ ለአለም ጤና ጥበቃ ዳይሬክተርነት እጩ ሆኖ ሲወጣ እንደ ትልቅ ገድል የተቆጠረለት የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ሆኖ ባገለገለባቸው አመታት አስመዝግቧል የተባለው የጤና መሻሻልና በውጪ ጉዳይ ሚንስትርነት አበርክቷል የተባሉት አስተዋጾዎች ናቸው።
ምዕራባዊያን ለጋሾች ለታዳጊ አገራት የጤና አገልግሎት በየአመቱ የሚሰጡትን ገንዘብ የሚመድበውና የመደበውን ገንዘብ ሥራ ላይ መዋሉን የመከታተል ሃላፊነት የተጣለበት ግሎባል ፈንድ የተባለው አለም አቀፍ ተቋም ቴዎድሮስ አድሃኖም የአገራችንን ጤና ጥበቃ ሚንስትር መሥሪያ ቤት በመራበት ወቅት ለነፍስ አድን ዕርዳታ ከሰጠው አንድ ቢሊዮን ሶስት መቶ ስድስ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ውስጥ ከፍተኛውን ገንዘብ እንዴት አድርጎ እንዳባከነና ለፖለቲካ ፍጆታ እንደዋለ በኦዲተሮቹ አስመርምሮ ይፋ አድርጓል።

ሜይ 14 ቀን 2012 ዓም ይፋ የሆነው ይህ የምርመራ ሪፖርት እንደሚያትተው በፈረንጆች አቆጣጠር 2009 እና 2010 ለአገራችን የተሰጠው የነፍስ አድን እርዳታ ገንዘብ ዋና አላማው በደማቸው ውስጥ የኤች አይቪ ቫይረስ የተገኘ ፤ በሳምባ ህመምና በወባ የተጠቁ ሰዎችን ህይወት ከሞት ለማትረፍ የታሰበና የገንዘብ ድልድሉም የሚከተለውን የሚመስል ነበር።

• ለሳምባና ወባ ህክምና 404 ሚሊዮን ዶላር
• ለኤች አይቪ 879 ሚሊዮን ዶላር
• የኤች አይቪ ተሸካሚዎች ኔት ዎርክ 9 ሚሊዮን ዶላር
• በኤች አይቪ በሽታ ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት መርጃ 14 ሚሊዮን ዶላር በድምሩ አንድ ነጥብ ሶስት መቶ ስድስት ሚሊዮን ዶላር

ከዜጎች ህይወትና ደህንነት በላይ የፖለቲካ ሥልጣን ዕድሜው እጅግ የሚያሳስበው የህወሃቱ ቴዎድሮስ አድሃኖም ግን ለነፍሰ አድን ከተሰጠው ከዚህ መጠነ ሰፊ ገንዘብ ውስጥ 165,393,027 /አንድ መቶ ስልሳ አምስት ሚሊዮን ሶስተ መቶ ዘጠና ሶስት ሺ ሃያ ሰባት/ የአሜሪካን ዶላር የለተቋሙ እውቅናና ፈቃድ 1309 ጣቢያዎችን አስገንብቻለሁ በማለት ገንዘቡን እንዳባከነ የግሎባል ፈንድ ኦዲተሮች ባደረጉት ምርመራ ደርሰውበታል። ከዚህም በተጨማሪ 57, 851, 941 ዶላር የት እንደገባ ማረጋገጫ አልተገኘለትም ።

የት እንደገባ ማረጋገጫ አልተገኘለትም የተባለውን ሃምሳ ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃምሳ አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ አርባ አንድ ዶላር ጉዳይ የሚያውቀው ቴዎድሮስ አድሃኖም ብቻ ሊሆን እንደሚችል ገምተን ወደ ጎን እንተወውና በእርዳታ ገንዘቡ ተገንብተዋል ስለተባሉት ጤና ጣቢያዎች ሪፖርቱ የሚያወራውን እንመልከት ። በግሎባል ፈንድ የኦዲት ሪፖርት መሠረት ቴዎድሮስ አድሃኖም 1309 ጤና ጣቢያዎችን በተቋሙ ገንዘብ ገንብተናል ብሏል።
ከነዚህ 1309 ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የግሎባል ፈንድ ኦዲተሮች 77ቱን እንዲጎበኝ ተደርጎ፤

• 71%ቱ ለጤና ጣቢያ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ የሆነውን የውሃ አገልግሎት በጭራሽ እንደሌለው፤
• 32%ቱ ሽንት ቤት የሚባል ነገር እንዳልተሠራለት፤
• 53%ቱ ገና ተሠርተው ከማለቃቸው የህንጻዎች ወለሎች በከፍተኛ ሁኔታ ተሰነጣጥቀው መገኘታቸውን፤
• 19%ቱ ደግሞ ጣራቸው ማፍሰስ መጀመራቸውን አረጋግጦአል።

የወያኔን ባለሥልጣናት የሞራልና የሙስና ዝቅጠት ደረጃ ግምት ውስጥ አስገብተን ይህንን የኦዲት ሪፖርት ማንበብ ከፈለግን እነዚህ ለጉብኝት ክፍት የሆኑት 77 ጣቢያዎች በተሻለ የጥራት ደረጃ ላይ ይገኛሉ ተብለው የተገመቱና በዚህም የተነሳ ቢጎበኙ ለጋሾች ተጨማሪ ዕርዳታ ሊሰጡን ይችላሉ አለያም ደግሞ በተሠራው ሥራ ያወድሱናል በሚል እምነት ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ለጉብኝት ክፍት ያልነበሩት ቀሪዎቹ 1232 ህንጻዎች በምን ሁኔታ ላይ ሊገኙ እንደሚችሉ ከዚህ በመነሳት ማወቅ ይቻላል። ጭራሽ የመሠረት ድንጋይ ሳይጣል ተሠርተዋል ተብለው ሪፖርቱ ውስጥ የተጠቃለሉ ሊኖሩ እንደሚችልም መጠርጠር አይከፋም ። የኛ ነው የሚሉትን የትግራይ ህዝብ ነፍስ ለመታደግ በዚያ በ1977ቱ የድርቅ ወቅት ከአለም ለጋሾች የተላከን የዕርዳታ እህል ሽጠው በምትኩ አሸዋ በጆንያ ሞልተው ሂሳብ ያወራረዱ ሽፍቶች የፈረንጅ እግር በማይደርስባቸው የአገሪቱ ክፍሎች የጤና ጣቢያ ህንጻዎችን አስገንብተናል ብለው ገንዘቡን ቢበሉት ምን ያስገርማል?

የግሎባል ፋንድ ኦዲት ሪፖርት ከላይ በተገለጸው ብቻ አላቆመም ። ድርጅቱ ለነፍስ አድን በሰጠው ገንዘብ ህክምና እርዳታ ይሰጥባቸዋል የተባሉና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ 46 የህክምና አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ጎብኝተው አብዛኛዎቹ የቧንቧ ውሃ አገልግሎት እንደሌላቸው፤ ለበሽታ ናሙና ምርመራ የሚጠቀሙባቸው ማይክሮስኮፖች የተበላሹና ያረጁ በመሆናቸው በተለይ የወባና የሳምባ በሽታን በትክክል ለመለየት የማያስችሉ መሆናቸውን ፤ በ46ቱም ተቋማት ውስጥ ካሉ ዶክተሮችና ነርሶች ስለወባ በሽታ ማኔጅመንት አንዳቸውም ሥልጠና አግኝተው እንደማያውቁ፤ ለህመምተኞች የሚሰጠው መድሃኒት መበላሸት ወይም አለመበላሸቱ በወቅቱ ቁጥጥር እንደማይደረግበት ወዘተ መታዘባቸውን አጋልጠዋል።

የኢትዮጵያዊያንን ህይወት ለማትረፍ ግሎባል ፈንድ የሰጠው ገንዘብ በዚህ መልኩ መባከኑንና በእርዳታ ስምምነቱ ውስጥ ላልተገለጸ አላማና ተግባር መዋሉን ካረጋገጠ ቦኋላ ተቋሙ እርምጃ ለመውሰድ የጀመረውን እንቅስቃሴ በወቅቱ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር የነበረው ሟቹ መለስ ዜናዊ ጣልቃ ገብቶ እንዳከላከለና ለግሎባል ፈንድ የገንዘብ ዕርዳታ ከሚለግሱ የአለም ዲታዎች አንዳንዶቹ የተለያየ ግፊት ፈጥረው ተድበስብሶ እንዲቀር እንዳደረጉት የሚያጋልጥ መረጃ በእጃችን አለ።

እንግዲህ ቴዎድሮስ አድሃኖም የጤና አገልግሎቶችን አስፋፍቶአል በማለት ለአለም ጤና ጥበቃ ዳይሬክተርነት እያደረገ ባለው ዘመቻ በመናፈስ ላይ ካለው የፈጠራ ህይወት ታሪክ በስተጀርባ ያለው እውነታ ይህ እንደሆነ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እናውቃለን። በዚህ ዘረፋ ምክንያት ህክምና አጥተው ህይወታቸው የተቀጠፈ ዜጎች ቁጥርም ውሎ አድሮ ጊዜ የሚያጋልጠው ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

ከዚህ ወንጀል በተጨማሪ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆኖ ባገለገለባቸው ጊዜያትም፡ ድርጅቱ ህወሃት በህዝባችን ላይ የፈጸማቸውን የጎዳና ላይ ጭፍጨፋዎች ፤ በየእስር ቤቱ በተወረወሩ የፖለቲካ እስረኞች ላይ የደረሰውን ሰቆቃና ግርፋት ፤ እንዲሁም እትብታቸው ከተቀበረበት ቦታ በጉልበት እንዲፈናቀሉ ተደርገው ለጎዳና ተዳዳሪነት የተዳረጉ በሺዎች የሚቆጠር ዜጎች ስቃይና መከራ ተሸፍኖ እንዲቀር የቻለውን ሁሉ አስተዋጾ አድርጎአል። የንቅናቄያችን ዋና ጸሃፊ የሆነውን ጓዳችን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን አየር ማረፊያ አሳፍኖ በመውሰድ ተግባር ውስጥም እጁ እንዳለበት እናውቃለን። የአጋዚ ጦር በቅርቡ በኢሬቻ በአል ላይ፤ በጎንደር፤ በባህርዳር ፤ በጌዶ ወዘተ የፈጸመውን ፋሽስታዊ ጭፍጨፋ ጀማሪ ዲሞክራሲ ስለሆን ህግ አስከባሪዎች በእውቀት ማነስ የፈጸሙት ነው በማለት እያናናቀ በተለያዩ አለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተዘባብቶብናል።

እንዲህ አይነት ወንጀለኛን የአፍሪካ አምባገነኖችና አንዳንድ ለሰው ልጆች ሰብዓዊ መብት ደንታ የሌላቸው የአገራቸውን ጥቅም ብቻ ለማስከበር ደፋ ቀና የሚሉ ምዕራባዊያን መንግሥታት አሞጋግሰው ለአለም ጤና ጥበቃ ዳይሬክተርነት ቦታ ቢያነግሱትም ባያነግሱትም ፍትህ እኩልነትና ነጻነት በምድራች ኢትዮጵያ እውን በሚሆንበት ቀን በግልና በቡድን ከፈጸመብን ወንጀል ተጠያቂነት ሊያድኑት እንደማይችሉ ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል።
የተባበሩት መንግሥታት አካል የሆነው የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት በእስከዛሬ ታሪኩ በሙያቸውና በሥነምግባራቸው የላቁ ሰዎችን እንጂ እንደ ቴዎድሮስ አድሃኖም ያሉ በሙያቸው የቀጨጩ ፤ ለፖለቲካ ፓርቲያቸው የሥልጣን ዕድሜ መራዘም ሲሉ ንጹሃንን በጠራራ ጸሃይ በማስጨፍጨፍ በሰው ደም የተጨማለቁ ወንጀለኞችን አስተናግዶ አያውቅም። ለንግዳቸው እንጂ ለጥቁር ህዝቦች ህይወት ደንታ የሌላቸው አለም አቀፍ ቱጃሮች እንደ ቴዎድሮስ አድሃኖም አይነት በጥቅም የሚገዛ ታዛዥ ሎሌ በቦታው ለማስቀመጥ እያደረጉ ያሉትን ሩጫ በቅርበት የሚከታተለው አርበኞች ግንቦት 7 የአለም ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የወንጀለኞች መደበቂያ ዋሻ ሊሆን እንደማይችል ይገነዘቡት ዘንድ ያሳስባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

ላፍንቴ 20 አመት በሚል ወያኔ ግንቦት 20ን ሊያከብር በደጋፊ አርቲስቶቹ ማስታወቂያ ሰርቶ ለቀቀ!!

አብዛኛው ሰው ልብ ያላለው ነገር አለ። እንደሚታወቀው የላፎንቴን 20ኛ አመት ላይ የሚሳተፉት አብዛኛዎቹ ዘፋኞች ከዚህ በፊት Boycott ስናደርግባቸው የነበሩት ናቸው!! ምክንያቱ ደግሞ ከነብሰ በላው ወያኔ ጋር እጅ እና ጓንት ሆነው ነው የሚሰሩት። ባለ ዝግጅቱን ታደለ ሮባን ጨምሮ ዲጄዎቹ ሁሉም ፣ጆኒ ራጋ፣ሀይሌ ሩት፣ሰይፉ ፋንታሁን እና አብዛኞቹ ከወያኔ ጋር ቁርኝት ያላቸው ናቸው!! ይህ ዝግጅት የሚዘጋጀው ለግንቦት 20 እንደሆነ አንዱ ዲጄ ነግሮኛል አብዛኛው ወጪ አሜሪካ ባሉት የትግራይ ማህበር የሚሸፈን ነው!! ቀኑን እራሱ ልብ ብላቹ ካያቹት May 27 ለሊት ነው፤ ይሄ ማለት የግንቦት 20 የዋዜማ ድግስ ነው፤ ዲሲ የሚገኘው ኢትዮጵያ ኢምባሲ ሊካሄድ የነበረውን የግንቦት 20 ዝግጅት ነው ወደ ላፎንቴን 20ኛ አመት የቀየሩት። ላፎንቴኖች አብረው መስራት ካቆሙ 10 አመት ሞልቷቸዋል ፤ ከተዋሃዱ ደግሞ 23 አመታቸው ነው!! እና በግንቦት 20 ቀን ሃያኛ አመት እናክብር ማለት ጤነኛነት ነው?? ከዚህ በኋላ እዚህ ዝግጅት ላይ የሚሳተፉትን ሁሉንም አዝማሪዎች Boycott እናረጋለን!!ቴዲ አፍሮ ተንኮላቸው ገብቶት አልታደምም ካላቸው ወር አልፎታል እነሱ ዛሬም ቴዲ አለ ብለው በስሙ ይነግዳሉ ፤ ቴዲ አፍሮ አይመጣም!! ይሄን የግንቦት 20 በአል የሚሳተፍ ሰው ከወያኔ ጋር እንዳበረ ይቁጠረው!! ከፈላስፋው ለሊበላ

ወያኔ በአዲስ አበባ ታክሲወች ላይ ያቀደው አደገኛ ሴራ ሲጋለጥ! – አስናቀው አበበ

የግል ትምህርት ቤቶች የስለላ መዋቅር እየተዘረጋላቸው ነው
አዲስ የገንዘብ ማካበቻ ዘዴ ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለስልጣን ቢሮ የከተማዋን ባለታክሲዎች ከስራ ውጪ ለማድረግ ያሴረው ውጥን እንደሚከተለው ነው…

የአ.አ. ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለስልጣን ቢሮ ከሚያዝያ 2009 ዓ.ም የመጨረሻ ሳምንት ጀምሮ እስከ 04/09/2009 ዓ.ም ድረስ በአጠቃላይ ለአፀደ ህፃናት እና ለ1ኛ/ደ/(ከ1-8) ት/ቤቶች በክፍያ ወደ ት/ቤት ለመሄድ እና ለመመለስ የተማሪዎች ትራንስፖርት ሰርቪስ/አገልግሎት እሰጣለሁ ብሏል፡፡ ለዚህም የፍላጎት መረጃ/Need assessment /ቅፅ ለሁሉም ት/ቤቶች በትኖ የተሞላውን መረጃ አሰባስቦ በቀጥታ ወደ ስራ እንደሚገባ ለየት/ቤቶች አሳውቋል፡፡ ይህ ድብቅና በተለይም ሁሉም የግል ት/ቤቶች ከተማሪ ወላጆች ጋር ስለፍላጎታቸው በቅርበት ያልተወያዩበት ጉዳይ መሆኑን ታውቆ ዋናው አላማውም የሚከተሉት ናቸው፡-
፨፨ መንግስት ገበያውን በብቸኝነት እና በበላይነት ተቆጣጥሮ በመቀጠል የእለት ኑሮአቸው እና ገቢያቸው ለተማሪዎች የትራንስፖርት ግልጋሎት በመስጠት የሚተዳደሩትን ባለታክሲዎች ሆን ተብሎ ለመጎድት
፨፨የከተማዋን ባለታክሲዎች በተለይም በአገልግሎት ቆይታቸው አርጅተዋል ተብለው ነገር ግን በአጭር ርቀትም ቢሆን እየሰሩ ያሉትን እና ሌሎችንም በትራንስፖርት ስምሪት ምድብ ውስጥ ገብተው መደበኛ አገልግሎት እየሰጡ
በተጨማሪ የእለት ኑሮን ለማሸነፍ ሲባል ጥዋትና ማታ ተማሪዎችን በኩንትራት ታክሲ የሚያመላልሱትን ከገበያ ለማስወጣት
፨፨ እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት ወያኔ ተተኪ ትውሉዱን በሚፈልገው የሪወት አለም ቅኝት እንዲራመድ በመንግስት ት/ቤቶች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ በየት/ቤቱ አንድ፡አንድ የአደረጃጀት ርዕሰ መ/ር ተብሎ ቅጥር በመፈፀም ዋና ተግባራቸው የድርጅት አባል ከመምህራን ፡ከአስተዳደር ሰራተኛውና ከተማሪዎች በመመልመል ርስበርስ አስተሳስሮ እንዲማቅቅ ያደረጉበትን ዘዴ ጠቀሜታ ስለሚያውቁት፡ነገር ግን በግል ት/ቤቶች ምንም አይነት መሠል መዋቅሮችን ስለማይከተሉ እና አመፅ ይኖራል ብሎ ስለሚያስብ፡የተማሪውን ስሜት፡ውሎና አቅጣጫ በቀላሉ ለመከታተል
፨፨ ወያኔ እያጣ የመጣውን የገንዘብ ገቢ መጠን ልክ በነጋዴው ማህበረሰብ ያለጥናት አዲስ የግብር ተመን ጥሎ ለመሠብሰብ ከሚኳትነው ተጨማሪ ዘዴም ነው ተብሏል፡፡
ለዘውትር አምደኛ ሪፖርተር እናመሰግናለን!
አስናቀው አበበ

ጋሹ እንዴት እንደተሰደደ? ከበውቀቱ ስዮም !!

ጋሹ እንዴት እንደተሰደደ? ከበውቀቱ ስዮም

(በ.ስ)

የዚች ጨዋታ መነሻ የሆነኝ የዛሬ ምናምን አመት ያነብኩት “ያረብ ሌሊቶች ” ተረት ነው::

ጋሹ ታታሪና አይናፋር ባላገር ነው:: ሲኖር ሲኖር; በስንት መከራ አንዲት ቆንጆ አጭቶ አገባ::

የሰርጉ ቀን ተበልቶ ተጠጥቶ ጭፈራው ደራ:: ሚዜዎችና አጃቢዎች ሙሽሮች እንዲጨፍሩ ጋበዙዋቸው:: ጋሹ ግብዣውን በስንት መግደርደር ተቀብሎ ይሄን እንቅጥቅጥ ያቀልጠው ጀመር:: ሰርገኛው ክብ ሰርቶ የሙሽራውን እስክስታ ባድናቆት ፈዝዞ መመልከት ጀመረ::

እንክሽ እነካ
እንክሽ እነካ
ይህንን ችሎታ- ደብቆት ነው ለካ!
እንክሽ እነካ
አብዮት ካሳነሽ- በጋሹ ተተካ😁

ህዝባዊ አድናቆቱ ብዙ አልቆየም:: ድንገት ከሙሽራው ሱሪ ግድም ቀለል ያለ ፍንዳታ ተሰማ:: የፍንዳታው መንስኤ በሙሽራው ሆድ ውስጥ ሲብላላ የቆየው 59 በመቶ ናይትሮጂን -21 በመቶ ሃይድሮጅን -9 በመቶ ካርቦን ዳይወክሳይድ -7 በመቶ ሜታን -የእስክስታውን ጫና መቁዋቁዋም አቅቶት አፈትልኮ መውጣቱ ነው::

ሙሽራው ክው አለ:: የሙሽሪትም ቆሌ ተገፈፈ
ሰርገኛው ሁላ ሳቁን ከጥቂት ሰከንዶች በላይ ማፈን አልቻለም::

በነጋታው: ጋሹ የፈሱን ሌጋሲ መሸከም ስላልቻለ ሙሽሪቱን ትቶ ከቀየው ተሰደደ:: አምስት አመት ሱዳን በስደት ማቀቀ::

ጊዜው እየጨመረ ሲሄድ ያገሩን ናፍቆት አሸነፈው:: እናም ለመመለስ ቆረጠ::

ድንበሩን ተሻግሮ ያገሩን ምድር ሲረግጥ እንዲት ሴትዮ የበቆሎ ጥብስ ስትሸጥ አገኛት:: ከሴትዮዋ አጠገብ ትንሽ ልጅ ቁጭ ብላ ጠጠር ትጫወታለች::

ጋሹ በቆሎ ገዝቶ ዝምብሎ እንዳይሄድ
“ይቺ ልጅ ስንት አመት ሆናት?” ብሎ ጠየቀ::
ሴትዮይቱ ትንሽ አሰቡና መለሱ-
” አመተምረቱ ትዝ አይለኝም! ብቻ ! ብቻ ሙሽራው ጋሹ በሰርጉ ቀን በፈሳ በሳምንቱ እንደተወለደች ትዝ ይለኛል”

ጋሹ እንደገና ተሰደደ::

እና እኔ እምላችሁ!

የድሜልክ ገድላችሁን -ባንድ ጀንበር ከሚረሳ
ያንዲት ቅፅበት ነውራችሁን -ለዘላለም ከሚያወሳ

ይሰውራችሁ!

አስቴር አወቀ ዳግም በሚኒሶታ ቦይ ኮት ተጠራባት !!!!

በአሜሪካ ግዛት የመጣችው አስቴር አወቀ ያስመጣት የወያኔ ፕሮመተሮች መሆናቸው ታወቀ ። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰውን የጭካኔ ግድያ ሲፈፅም የነበረው የትግራይ ነፃ አውጪ ወያኔ  የምርት ድርጅቱን ማንኛውንም የወያኔ መገልገያ ላለመጠቀም። ህዝብ ቦይ ኮት መጥራቱ አይዘነጋም።ሆኖም ወያኔ ምርቱ በበቂ ሆኔታ ባለመሸጡ ለአርቲስቶች ዳጉስ ያለ ገንዘብ በመክፈል ቢራቸው እንዲሸጥ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል ።በተለይ በባህር ዳር የቢራውን ስም በመቀየር ባላገሩ ቢራ ብለው ህዝብን በመናቅ ከአርቲስቶች ጀርባ የተደበቀውን ወያኔ ገሀድ የወጣበትን አርቲስት ኩኩ የተካፈለችበት የባህር ዳሩ ኮንሰርት በቦንብ ፍንዳታ መቃረጡ ይታወቃል ። ይሆንና የወያኔ ፕሮሞተሮች ሲያትል ላይ ያስመጣትን አስቴር አወቀን የማስታወቂያ ቪድዮ ሰርተው አስቴርን ጠይቀዋታል አስቴርም የህዝብ ነኝ ስትል ተናግራለች ይሁንና አንዳንድ አስተያየት ሰጪወች የህዝብ ነኝ እየተባለ ከወያኔ ጋር መሞዳሞድ ተገቢ እንዳልሆነ ገልፀዋል ሰው የሚለካው ሰውነቱ በስራው ነው ብለዋል ።ይህ በእንዲህ እንዳለ   የስርአቱ ደጋፊወች ብቻ ገብተው በሲያትሉ ኮንሰርት ላይ መመልከታቸውን ከስፍራው ተመልክተናል አሁንም በድጋሚ ሚኒሶታ ላይ የተጠራው ልማታዊ ኮንሰርት ቦይ ኮት በድጋሚ እንደተጠራበት ለማወቅ ተችላል የህዝብ ደም እንደጉድ በፈሰሰባት ኢትዮጵያ ከትግራይ ነፃ አውጪ የባርነት አገዛዝ ነፃ እስክንወጣ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላ ሲሉ በሚንሶታ የሚገኙ ቦይኮት የጠሩ አካሏት ተናግረዋል ።

 

Ethiopian news archieves